1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰላም ባንክ ምስረታ በሀዋሳ 

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 28 2013

ባለፈዉ ማክሰኞ በይፋ የተመሠረተዉ ማዕከል የተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢን በሚያዉከዉ ግጭትና ጥቃት ሰበብ የደፈረሰዉን ሠላም ለማጥራትና ለማርጋት  የሚደረጉ ጥረቶችን ያግዛል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል።

https://p.dw.com/p/3t49T
Äthiopien Gründung einer "Friedens-Bank" in Hawassa
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

የሰላም ባንክ ዓላማና ፋይዳዉ


በኢትዮጲያ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚረዱ የመፍትሄ ሀሳቦችን የሚያሰባስብ፣ የሚያከማችና ሥራ ላይ የሚያዉል «የሰላም ባንክ» የተባለ ማዕከል አዋሳ-ዉስጥ  ተመሰረተ ። ባለፈዉ ማክሰኞ በይፋ የተመሠረተዉ ማዕከል የተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢን በሚያዉከዉ ግጭትና ጥቃት ሰበብ የደፈረሰዉን ሠላም ለማጥራትና ለማርጋት  የሚደረጉ ጥረቶችን ያግዛል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል።በአንድ ግለሰብ ሐሳብ አመንጪነት የተመሰረተዉ የሰላም ባንክ ዘር፣ ፆታ፣ እድሜና የትምሕርት ደረጃ ሳይለይ ሁሉንም ኢትዮጵያ በአባልነት የሚያቅፍ እንደሆነ ተነግሯል።

ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ