1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ የሰላም ምክክር መድረክ

ዓርብ፣ ኅዳር 12 2012

በመላ ሃገሪቱ የሚገኙ የፀጥታ አካላት በሀገሪቱ የተከሰተዉን የሰላም መደፍረስ ሕዝብን ባሳተፈ መልኩ ለመፍታት በንቃት መንቀሳቀስ እንዳለባቸዉ የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈርያት ካሚል አሳሰቡ። የምክክር መድረኩ ለሦስት ቀናት ይዘልቃል።

https://p.dw.com/p/3TY1R
Äthiopien | Logo  Ministry of Peace
ምስል DW/G. Tedla

መድረኩ ለሰላም የምሰራዉን የምንሰንቅበት ነዉ

በመላ ሃገሪቱ የሚገኙ የፀጥታ አካላት በሀገሪቱ የተከሰተዉን የሰላም መደፍረስ ሕዝብን ባሳተፈ መልኩ ለመፍታት በንቃት መንቀሳቀስ እንዳለባቸዉ የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈርያት ካሚል አሳሰቡ። ሚኒስትሯ በመሥርያ ቤታቸዉ በኩል በተዘጋጀዉ እና ከመላዉ ሀገሪቱ የተዉጣጡ የፀጥታ ኃላፊዎች የተሳተፉበት የሰላም ምክክር መድረክ ላይ ተገኝተዉ እንደተናገሩት ፖሊስን የማዘመን ሥራ እየተሰራ እንደሆን ገልፀዋል። «መድረኩ ሁለት አይነት ባሕሪ ያለዉ መድረክ ነዉ። የመጀመርያዉ አሁን የምንገኝበትን ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ የምንገመግምበት፤ በሌላ መልኩ በቀጣይ ለምንሠራቸዉ ሥራዎች ስንቅ የምንሰንቅበት» ሲሉ ነበር የሰላም ሚኒስትሯ የዉይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት ። ሐሙስ የጀመረዉ የሰላም ምክክር መድረክ ለሦስት ቀናት እንደሚዘልቅ ታዉቋል።  

ዮሃንስ ገብረግእግዚአብሔር


አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ