የሩስያ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ
ሰኞ፣ መጋቢት 10 2010ማስታወቂያ
ትናንት በተካሄደዉ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ያሸነፉት ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን የጦር መሳሪያ ፉክክር የማካሄድ ሀሳብ እንደሌላቸዉ ተናግረዋል። ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክትም ከሌሎች ሃገራት ጋር ያላቸዉን ልዩነትም ለመፍታት እንደሚሰሩም ገልጸዋል። የምርጫዉ ዉጤት ከተሰማ በኋላ የቻይናዉ አቻቸዉ ሺ ዢንፒንግ የእንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት ሲልኩ፤ የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ማኑዌል ማክሮ በበኩላቸዉ ሩሲያን በፖለቲካ፣ ኤኮኖሚ፣ ዴሞክራሲ እና ማኅበራዊ ረገድ ለማዘመን እንዲሳካላቸዉ ተመኝተዉላቸዋል። የአዉሮጳ የፀጥታ እና የጋራ ትብብር ድርጅት በበኩሉ ምንም እንኳን ሕጋዊ የምርጫ ሂደት መኖሩን ቢታዘብም እዉነተኛ ፉክክር እና እዉነተኛ አማራጭ አልነበረም ሲል ተችቷል። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የሩሲያን ምርጫ ከ1,300 የሚሆኑ ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች ተገኝተዉ ተከታትለዋል።
ገበያው ንጉሤ
አርያም ተክሌ
ሂሩት መለሰ