የረሐብ አድማና ተቃውሞ በቂሊንጦ እስር ቤት
ዓርብ፣ ሐምሌ 6 2010ማስታወቂያ
በአሸባሪነት ተከሰው በቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙ ሰዎች ከትላንት ጀምሮ የረሐብ አድማ ላይ መሆናቸው ተነገረ። እስረኞቹ፦ ግንቦት 7 እና ኦነግ የአሸባሪነት ክስ እና ፍረጃ ሲነሳላቸው ፣በአሸባሪነት ተከሰው የነበሩ ግለሰቦችም ሲፈቱ የእኛን ጉዳይ የሚመለከት ጠፍቷል በሚል ምሬት የረሐብ አድማ መጀመራቸውን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ተናግረዋል።
ከታሳሪ ቤተሰቦች በተገኘ መረጃ መሰረት፦ ከረሐብ አድማው በኋላ «ብሉ አትብሉ» በሚል በተነሳው ተቃውሞ ፖሊስ አስለቃሽ ጢስ እንደተኮሰ እና ወደ ሦስት የሚጠጉ እስረኞች ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል ። በሽብር ለተከሰሱ ስድስት መቶ እስረኞች ነጻ የጥብቅና አገልግሎት የሰጡ እና በአሁኑ ወቅት ወደ 80 ለሚጠጉ በአሸባሪነት ለተከሰሱ እስረኞች ጥብቅና የቆሙት ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳ የደንበኞቻቸው ቤተሰቦች የነገሯቸውን ለዶቼቬለ አስረድተዋል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ