1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርትአፍሪቃ

«የሥራ ገበያ » ዐውደ ርዕይ በሐዋሳ

ረቡዕ፣ መስከረም 12 2014

በኢትዮጲያ በየዓመቱ ከዩኒቨርስቲዎች የሚመረቁ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን የመቀጠር ምጣኔ ለማሳደግ ያስችላል የተባለ የስራ ገበያ አውደ ርዕይ እየተካሄደ ይገኛል ። በሀዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የሥራ ገበያ  አውደ ርዕይ ቀጣሪ ድርጅቶችን ከተመራቂዎች ጋር ለማገናኘት እንደሚያስችል ተነግሮለታል።

https://p.dw.com/p/40ev3
Äthiopien | Job Market in Hawassa
ምስል Shewangizaw Wegayehu

«የሥራ ገበያ » ዐውደ ርዕይ በሐዋሳ ተከፈተ

የሥራ ገበያ

በኢትዮጲያ በየዓመቱ ከዩኒቨርስቲዎች የሚመረቁ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን የመቀጠር ምጣኔ ለማሳደግ ያስችላል የተባለ የስራ ገበያ አውደ ርዕይ እየተካሄደ ይገኛል ።

በሀዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የሥራ ገበያ  አውደ ርዕይ ቀጣሪ ድርጅቶችን ከተመራቂዎች ጋር ለማገናኘት እንደሚያስችል የአውደ ርዕዩ ተሳታፊዎች ለዶቼ ቬለ (DW) ገልጸዋል።

በአውደ ርዕዩ 35 ቀጣሪ ድርጅቶች መሳተፋቸውን የጠቀሱት የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር መሳይ ሀይሉ ይህም ለዩኒቨርሲቲው ምሩቃን ልዩ እድል የሚፈጥር ነው ብለዋል ።

 ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ 

ታምራት ዲንሳ

ማንተጋፍቶት ስለሺ