የሥራ እድል ፈጠራ በኢትዮጵያ
ሰኞ፣ ጥር 18 2012ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግስት ባለፉት ስድስት ወራት ለ1.1 ሚልዮን ዜጎች ስራ መፍጠሩን አስታወቀ፡፡ የስራ እድል ከተፈጠረባቸው ዘርፎች መካከል የግብርና፤ የኢንዱስትሪ እንዲሁም የግል እና የመንግሥት አገልግሎት ዘርፎች ትልቁን ቦታ እንደሚይዙ ገልጿል። ሆኖም የተፈጠረው ስራ ከተያዘው ዕቅድ አንፃር ያነሰ መሆኑን የኢትዮጵያ ስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ለዜጎች በርካታ ስራ እንዳይፈጥር ዕንቅፋት ተብለው ከተጠቀሱት መካከል ነው፡፡ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ ከመቀሌ ዝርዝር ዘገባ አለው።
ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ