1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሞጆ ሐዋሳ የፍጥነት መንገድና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ

ረቡዕ፣ መጋቢት 2 2012

የሞጆ ሐዋሳ  የፍጥነት መንገድ በተለይ እስከ መቂ ድረስ ያለው ከ80 በመቶ በላይ ተጠናቆ ግንባታው በመከናወን ላይ ይገኛል። ወደ ግንባታው የተገባው በአራት ምዕራፍ ተከፍሎ እንደኾነ የተገለጠለት ይኽ የፍጥነት መንገድን በፍጥነት ገንብቶ ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ መኾኑ ተገልጧል።

https://p.dw.com/p/3ZEpB
Wegweiser Autobahnschild Äthiopien
ምስል DW

የሞጆ ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ

የሞጆ ሐዋሳ  የፍጥነት መንገድ በተለይ እስከ መቂ ድረስ ያለው ከ80 በመቶ በላይ ተጠናቆ ግንባታው በመከናወን ላይ ይገኛል። ወደ ግንባታው የተገባው በአራት ምዕራፍ ተከፍሎ እንደኾነ የተገለጠለት ይኽ የፍጥነት መንገድን በፍጥነት ገንብቶ ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ መኾኑ ተገልጧል። የመንገድ ግንባታው  ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና ሃገራት በተገኘ ብድር መኾኑም ተጠቅሷል። ኢትዮጵያን ከጎረቤት ሃገራት ለሚያገናኙ 9 የመንገድ ፕሮጀክቶች በድምሩ ከ25 ቢሊዮን በላይ ብር መመደቡ ይነገራል። በሀገሪቱ እየተገነቡ ስለሚገኙ ሀገር አቋራጭ መንገዶችን በተመለከተ ለሚቃኘው ከኢኮኖሚው ዓለም መሰናዶ ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ማንተጋፍቶት ስለሺ