1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምዕራብ ጎንደር ወቅታዊ ሁኔታ

ሰኞ፣ ጥር 6 2011

በምዕራብ ጎንደር ሰሞኑን የተከሰተው ግጭት መሻሻል ቢተይበትም አሁንም ችግሩ እንዳልተወገደ የአማራ ክልል መንግስት አስታወቀ፡፡ የአማራ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ ዛሬ በክልሉ ወቅታዊ ጉዳች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

https://p.dw.com/p/3BXLp
Asemahegn Aseres
ምስል DW/A. Mekonnen

የምዕራብ ጎንደር ወቅታዊ ሁኔታ

 አቶ አሰማኸኝ አስረስ በመግለጫቸው በምእራብ ጎንደር በአማራና በቅማንንት መካከል ከሀምሌ 2010 ዓ ም ጀምሮ በአካባቢው አለመረጋጋት ተፈጥሮ ህይወት  መጥፋቱን ተናግረዋል፡ የችግሩን መጠንና አጠቃላይ ጉዳዩን የሚያጠና ግብረሀይል ወደቦታው መጓዙን የተናገሩት ዳይሬክተሩ ርእሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸውም ወደ ቦታው በመሄድ ከህዝቡ ጋር መወያየታቸውን አመልክተዋል፡፡ ርእሰ መስተዳድሩ በወቅቱ የመኪና አደጋ ደርሶባቸዋል የሚባለውወሬም ፍፁም ሀሰት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አንደዚሁም አመራር ተጠራርጎ ይውረድልን የሚሉ ጥያቄዎች በየአካባቢው እተነሳ መሆኑን የተናገሩት አቶ አሰማኸኝ ይህም ስርኣትን ጥብቆ የሚሄድ እንጂ በዘፈቀደ የሚፈፀም አይደለም ብለዋል፡፡ ከቡሌ ሆራ ኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር በተያያዘ ጉዳዩ በፌደራል መንግስት እንደሚመለስ አስረድተዋል፡፡ እህል የጫኑ መኪናዎች አያልፉም በሚል እየተደረገ ያለው ድርጊት ህገወጥ በመሆኑ ሊታረም እንደሚገባም አሳስበዋል።
ኣለምነው መኮንን

አርያም ተክሌ

ተስፋለም ወልደየስ