የምዕራባዉያን መሪዎች ጉባኤ
ሐሙስ፣ መጋቢት 15 2014ማስታወቂያ
ዩናይትድ ስቴትስ የምትመራና የምታስተባብራቸዉ የተለያዩ ማሕበራት አባል ሐገራት መሪዎች ዛሬ ብራስልስ-ቤልጂግ ዉስጥ ጉባኤ ተቀምጠዋል።የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO)፣ የአዉሮጳ ሕብረትና የቡድን ሰባት (G7) አባል ሐገራት መሪዎች የጀመሩት ጉባኤ አብይ ትኩረት የዩክሬንና የሩሲያ ጦርነት ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ መከላከል ነዉ።ጉባኤተኞች የኔቶ አባል በሆኑ የምሥራቅ አዉሮጳ ሐገራት ተጨማሪ የአሜሪካ ጦር እንዲሰፍር ይወስናሉ ተብሎም ይጠበቃል።
ገበያዉ ንጉሴን
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ