1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

የምዕራቡ ዴሞክራሲ ወዴት?

እሑድ፣ ጥር 16 2013

አራቱን የሥልጣን ዘመናቸውን በውዝግብ ያሳለፉት 45ኛው የአሜሪካን ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ውጤት አልተሸነፍኩም በሚለው አቋማቸው እንደጸኑ በሀገሪቱ ባልተለመደ መልኩ ነው ከነጩ ቤተ መንግሥት ሳይወዱ በግድ የወጡት።

https://p.dw.com/p/3oJEN
USA | Präsidentschaftswahl | Demonstranten im Capitol
ምስል Lev Radin/Pacific Press/picture alliance

«አሜሪካ ዴሞክራሲን ለመስበክ በቀጣይ ትችል ይሆን?»

በመላው ዓለም የዴሞክራሲ ተምሳሌት ተደርጋ በምትወሰደው ዩናይትድ ስቴትስ ከሳምንታት በፊት የታየው ሥልጣንን በአመፅ የማስቀጠል ሙከራ ብዙዎችን አስደምሟል። አራቱን የሥልጣን ዘመናቸውን በውዝግብ ያሳለፉት 45ኛው የአሜሪካን ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ውጤት አልተሸነፍኩም በሚለው አቋማቸው እንደጸኑ በሀገሪቱ ባልተለመደ መልኩ ነው ከነጩ ቤተ መንግሥት ሳይወዱ በግድ የወጡት። ታኅሣሥ 28 ማለትም በጎርጎሪዮሳዊው ቀመር ጥር 6 2021ዓ,ም ለአመፅ የቀሰቀሷቸው ደጋፊዎቻቸው የወሰዱት የኃይል ርምጃ በቀላሉ ባይቀለበስ ኖሮ ዛሬ ሀገሪቱ ስለዴሞክራሲ ማውራት ከማትችልበት ደረጃ በደረሰች ነበር። ከውጥንቅጡ ያተረፏት ጠንካራ ተቋማት መገንባቷ ነው የሚሉ እንዳሉ ሁሉ፤ ተቋማትማ በየሃገራቱ አሉ፤ አሜሪካን የሚለያት ሕግ የሚተገበርባት ሀገር በመሆኗ ነው በማለት የሚሟገቱም አሉ። ይህም ሆኖ ካፒቶል ኺል ላይ የተፈጠረው ዴሞክራሲን የመቀልበስ ሙከራ በሌሎች ላይ ምን ተፅዕኖ ይኖረው ይሆን? የምዕራቡ ዴሞክራሲ ወዴት? ሙሉ ውይይቱን ከድምጽ ዘገባው ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ