የምክር ቤቱ የመጪው ዓመት የበጀት ውይይት
ማክሰኞ፣ ሰኔ 8 2013ማስታወቂያ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2014 ዓ,ም የፌደራል መንግሥት በጀት ላይ ዛሬ ተወያየ። ምክር ቤቱ የመጪው ዓመት በጀት አምስት መቶ ስልሳ አንድ ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር እንዲሆን በመወያየት ለዝርዝር እዕታ ለበጀት ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቶታል። የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ለምክር ቤቱ እንደተናገሩት በለጋሽና የልማት አጋሮች በኩል ጫና እና ማዘግየት ቢኖርም እስካሁን የደረሰ የገንዘብ ክልከላ የለም ብለዋል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሰ