የምርጫ ጊዜ ዉዝግብ
ዓርብ፣ ሐምሌ 26 2011ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ የሚደረግበት ጊዜ የሐገሪቱን ፖለቲከኞች አሁንም እያወዛገበ ነዉ። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ትናንት በሰጡት መግለጫዉ ሥለ ምርጫዉ ጊዜ ቁርጥ ያለ መልስ አለመስጠታቸዉ ዉዝግቡ እልባት እንዳያገኝ አድርጎታል። ምርጫዉ ከዚሕ ቀደም በተያዘዉ የጊዜ ሠለዳ መሠረት በመጪዉ ዓመት ግንቦት አካባቢ መደረግ አለበት-የለበትም የሚል ተቃራኒ አቋም ከያዙ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች የሁለቱ ተወካዮች ዛሬ እንዳሉት የጠቅላይ ሚንስትሩ መግለጫ አሻሚ ነዉ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አዲስ ያረቀቀዉን የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲ አደረጃጀት ሕግን 33 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትናንት በይፋ ተቃዉመዉታል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ