1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምርጫ ዝግጅት በአሶሳና ካማሺ ዞን 

ማክሰኞ፣ ሰኔ 8 2013

ስድስተኛውን የሀገር አቀፍ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ከ30 ሚሊዩን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫው ጠቁመዋል፡፡  ከእነዚህም  በተጨማሪም የመራጮች ምዝገባ ያልተካደባቸው አካባቢዎች እና በሰኔ 14/2013 ዓ.ም ምርጫ የማካሄድባቸውም ስፋራዎችም በርካቶች መሆናቸው ተገልጸዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3uxTL
Asosa, West-Äthiopien und Hauptstadt der Region Benishangul-Gumuz
ምስል privat

የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ጳጉሜ 1ቀን 2013 ዓ.ም ይከናወናል ተብሎአል፡፡

ስድስተኛውን የሀገር አቀፍ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ከ30 ሚሊዩን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫው ጠቁመዋል፡፡  ከእነዚህም  በተጨማሪም የመራጮች ምዝገባ ያልተካደባቸው አካባቢዎች እና በሰኔ 14/2013 ዓ.ም ምርጫ የማካሄድባቸውም ስፋራዎችም በርካቶች መሆናቸው ተገልጸዋል፡፡  በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ የወለጋ ዞኖች አምስት በሚደደረሱ የምርጫ ጣቢዎች  ምርጫ በሰኔ ወር እንደማይካድም የምርጫ ቦርድ መግለጫ ያሳያል፡፡፡፡ ምርጨ ካርድ የወሰዱ የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች  ይወክለናል የሚሉትን ለመምረጥ ዝግጁ መሆናቸው የተናሩ ሲሆን በተለያዩ ግጭቶች ተፈናቅለው በምእራብ ወለጋ የሚገኙ ነዋሪዎች ደግሞ  የአካባቢው ሰላም ተረጋግጠው ወደ  ቀድመው ቀአቸው መመለስ እንደሚፈልጉና  የእለት ደራሽ ድጋፍ ወቅቱን ጠብቀው እንዲደርሳቸው ሀሳብ አቅርበዋል፡፡
በቀጣይ ሳምንት ሰኞ ሰኔ 14/2013 በሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ምርጫ በሚካሄድባቸው የአሶሳና አሶሳ ዞን ወረዳዎች ከ360ሺ በላይ ዜጎች የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን የምርጫ ቦርድ መረጃ ያመለክታል፡፡ አቶ ሙላቱ ክፍሌ የአሶሳ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ  በሀገራዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ የምርጫ ካርድ ካወጡት መካከል ናቸው፡፡ ዘንድሮ ለ3ኛ ጊዜ በምርጫ እንደሚሳፉ የተናገሩት አቶ ሙላቱ  ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆንና ከምርጫው በኀላም በሀገሪቱ ሰላም ይሰፍናል የሚል እምነት እንዳላቸው አስታውቋል፡፡
አቶ  ማቲዩስ ታከለ ደግሞ በሚያዚያ ወር ከካማሺ ዞን የተፈናቀሉ  ሲሆን  በምዕራብ ወለጋ መንዲ ከተማ ይገኛሉ፡፡ ቀድሞ ከነበሩት ስፋራ በነበረው ግጭት ለበርካታ ዓመት ከኖሩበት ሰዳል ወረዳ ሸሽተው በጊዜአዊ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ሲሆን በሀገራዊ ምርጨ ለመሳፍ እድሉን እዳላገኙም ገልጸዋል፡፡ ከሀገራዊ ምርጫም በኀላም ሰላም ሰፍኖ ወደ ቀድሞ ቀአቸው ለመመስ ፍላጎት እንዳቸው አመልክቷል፡፡  በተጠለሉበት ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያም ሆነው በምርጫ ለመሳተፉ ፍላጎት እንደነበራቸው እና |የምርጫ ካርድ ለማውጣት የከተማው ነዋሪ መሆን አለባችሁ በመባላቸው እንዳልተሳካቸውም ተናግረዋል፡፡
የግብርና ባለሙያ የሆኑት አቶ  በቀለ ተስፋሁን ይሰሩበት ከነበረው ካማሺ ዞን ሰዳል ወረዳ ከተፈናቀሉ ሁለት ወር እንደሆናቸው ተናግረዋል፡፡ አሁን ባሉበት ምዕራብ ወለጋ ማናስቡ ወረዳ  ከ4ሺበላይ ተፈናቃዩች እንዳሉም በመጥቀስ  ወደ ነበሩበት አካባቢ ለመመስ  ፍላጎት እደለላቸው ገልጸው ከተፈናቀሉበት አካባቢ የጸጥታ ሁኔታም በምርጫ ለመሳፍ አመቺ አለመሆኑን አክልዋል፡፡ 
የብሔራዊ ምርጫ ቦርደ ሰኔ 3 ባወጣው መግለጫውም  በተለያዩ  ምክንያቶች  ሰኔ 14 ሀገራዊ ምርጫ የማይካሄድባቸው በምዕራቡ ኢትዩጵያ የሚገኙ  ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ  ክልል መተከል ዞንና ካመሺ ዞን እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል ወለጋ  ዞኖች ስድስት የሚደርሱ ጣቢያዎች  የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ጳጉሜ 1 /2013 ዓ.ም እንደሚከናወን አሳታውቋል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ
አዜብ ታደሰ 

ሸዋዬ ለገሰ