1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምርጫ ክርክር የአየር ጊዜ በታዛቢዎች እይታ

ዓርብ፣ ሰኔ 11 2013

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ለፖለቲካ ፓርቲዎች በነፃ የደለደሉት የዓየር ሰአትና የጋዜጣ አምድ መራጩ ሕዝብ ግንዛቤ እና መረጃ በተሻለ እንዲያገኝ ያገዘ ነበር ተባለ። በነፃ የመገናኛ ብዙኃን የቅስቀሳ መርኃ-ግብር ላይ ከፍትኃዊነትና ሚዛናዊነት ጋር በተያያዘ የተወሰነ የፓርቲዎች ቅሬታ እንደነበራቸው ሲገልፁ ነበር።

https://p.dw.com/p/3v9rx
Logo | National Election Board of Ethiopia
ምስል National Election Board of Ethiopia

የተወሰነ የፓርቲዎች ቅሬታ እንደነበራቸው ሲገልፁ ነበር

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ለፖለቲካ ፓርቲዎች በነፃ የደለደሉት የዓየር ሰአት እና የጋዜጣ አምድ መራጩ ሕዝብ ግንዛቤ እና መረጃ በተሻለ እንዲያገኝ ያገዘ ነበር ተባለ። ለሁለት ወራት በቆየው ነፃ የመገናኛ ብዙኃን የቅስቀሳ መርኃ-ግብር ላይ ከፍትኃዊነት እና ሚዛናዊነት ጋር በተያያዘ የተወሰነ የፓርቲዎች ቅሬታ እንደነበራቸው ሲገልፁ ነበር። ሆኖም ክልላዊ ፓርቲዎች የተሰጣቸውን እድል በአግባቡ እንዳልተጠቀሙበት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ተናግሯል።ያነጋገርናቸው ሁለት የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶችም ሒደቱ የተለያዩ የፍትኃዊነትና የሚዛናዊ አጠቃቀም ችግሮች የነበሩበት ቢሆንም መልካም ውጤት ያለውና ለወደፊት ምርጫዎችም ትልቅ መሠረት ጥሎ ያለፈ ነበር ብለዋል። ለዚህ ተግባር በ57 የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ላይ 46 የፓለቲካ ፓርቲዎች አገልግሎት ማግኘታቸው ተነግሯል።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሰ