1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምርጫ ቦርድ ለመገናኛ ብዙኃን የዘገባ ፈቃድ እየሰጠ ነው

ሐሙስ፣ መጋቢት 30 2013

ከሁለት ወራት ያነሰ ጊዜ የቀረውን ስድስተኛውን ጠቅላላ አገር አቀፍ ምርጫ ለመዘገብ እስካሁን 21 የሀገር ውስጥ እና  ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንና 800 ጋዜጠኞች የዘገባ ፈቃድ መሰጠቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አስታውቋል። መስፈርቱን  ለሚያማሉ የመገናኛ ብዙኃን በቀጣይም ፈቃድ መስጠቱን እንደሚቀጥል ቦርዱ ገልጿል።

https://p.dw.com/p/3riyd
Äthiopien | Presseausweis
ምስል Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ለመገናኛ ብዙኃን ፈቃድ እየሰጠ ነው

ከሁለት ወራት ያነሰ ጊዜ የቀረውን ስድስተኛውን ጠቅላላ አገር አቀፍ ምርጫ ለመዘገብ እስካሁን ሃያ አንድ የሀገር ውስጥ እና  ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንና 800 ጋዜጠኞች የዘገባ ፈቃድ መሰጠቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አስታውቋል። መስፈርቱን  ለሚያማሉ ቀሪ የመገናኛ ብዙኃን እና ጋዜጠኞችም በቀጣይም ፈቃድ መስጠቱን እንደሚቀጥል ቦርዱ ገልጿል።
መገናኛ ብዙኃኑ የመረጃ ፍሰት እጥረት እንዳይገጥማቸው የሚዲያ ማዕከላት በቀጣይ ቀናት ተከፍተው አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ እያመቻቸ መሆኑንም ነው ቦርዱ በተለይ ለዶይቼ ቬለ የገለጸው። ፍቃድ የተሰጣቸው የመገናኛ ብዙኃኑ ኃላፊነት በተሞላበትና ከፍተኛ ጥንቃቄ ባለው መልኩ መረጃዎችን ለሕዝብ እንዲያቀርቡ ይደረጋልም ተብሏል።
ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ
ኂሩት መለሰ