1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምሥራቅ ኢትዮጵያ የፀጥታ ውይይት መድረክ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 25 2011

በምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች በየጊዜው በሚነሳው ግጭት ሳቢያ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ የሚደርስ ጉዳትም ሆነ የዜጎች መፈናቀል አልቆመም፡፡ በአካባቢው ባለው ሕገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ የሚዘዋወረው ሕገወጥ መሳርያ እና ሕገወጥ ገንዘብም ለአካባበቢው ሰላም መደፍረስ ተግዳሮትነቱ እንደቀጠለ ነው።

https://p.dw.com/p/3Azt3
Äthiopien Konferenz des Sicherheitschefs in Dire Dawa
ምስል DW/M. Teklu

የምስራቅ ኢትዮጵያ የፀጥታ ውይይት መድረክ

በምሥራቅ የአገሪቱ አካባቢዎች ዛሬም ድረስ ስር ነቀል መፍትሄ አግኝቶ መብረድ ያልቻለውን ግችት ማቆም እና ችግሩን መፍታት ያልተቻለበትን ምክንያት ምንነት ጠለቅ ብሎ ለመመርመር ትናንት በድሬደዋ የተካሄደው የምሥራቅ ኢትዮጵያ  አጎራባች ክልሎች የፀጥታ ውይይት መድረክ  በርካታ  ሀሳቦች ተነስተውበታል ፡፡በየጊዜው የአካባቢውን የፀጥታ ሥራ በዕቅድ ለመምራት ጥረት ቢደረግም ወደ አፈፃፀም ሲሸጋገር ችግሮች ማጋጠማቸው በመድረኩ ተነስቷል ፡፡  የሀገር መከላከያ ምሥራቅ ዕዝና የፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች የፀጥታ እቅዱን ተግባራዊ ከማድረግ ጎን ለጎን ተጠያቂ የሚያደርግ አሰራር አለመኖሩ ዋና ችግር መሆኑን አንስተዋል ፡፡በዚህም አመራሩ ሀላፊነት ወስዶ መስረት ከራሱ መጀመር እንዳለበት ነው የጠቆሙት ፡፡በየአካባቢው እየተነሱ ያሉ ግጭቶችንና አሁን ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በጥልቀት የመረመረው የውይይቱ መድረክ ዋነኛ ያለውን የተጠያቂነት አሰራር አለመኖር ችግር ለመቅረፍ የሚረዳ በየደረጃው የዕቅድ አፈፇፀምን ለመገምገምና ተጠያቂነት ማስፈን የሚያስችል አዲስ የአሰራር ስርዓት አስቀምጧል ፡፡ለዚህም ኮሚቴዎችን አዋቅሯል፡፡የመከላከያ ዕዝ ከፍተኛ አዛዦች፣ የፌደራል ፖሊስና የክልል የፀጥታ ሃላፊዎች የተገኙበት ይህ መድረክ ያስቀመጠው አሰራር በአካባቢዎቹ ግጭትን በማስቆም ፣ የዜጎች መፈናቀልን በማስቀረት፣ ሕገወጥ የየንግድ እንቅስቃሴውን በማስቆም እና የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ በማደራጀት ሰላምን በዘላቂነት ለማስፈን  አዲስ ተስፋ ተጥሎበታል ፡፡  

መሳይ ተክሉ

አርያም ተክሌ

ማንተጋፍቶት ስለሺ