1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሜርክል ጥሪ 

ሐሙስ፣ ሐምሌ 2 2012

ሜርክል በብራሰልሱ የአውሮጳ ህብረት ፓርላማ ባሰሙት ንግግር ህብረቱ አሁን ከጋጠመው ቀውስ ሊወጣ የሚችለው በአንድነትና በመተባበር እንደሆነ አስገንዝበዋል።ሜርክል በብራሰልስ ቆይታቸው አባል ሃገራት ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን በመተው የህብረቱ ያወጣው የ750 ቢሊዮን ዮሮ ከኮቪድ 19 ማገገሚያ እቅድ ተቀብለው እንዲያጸድቁ ጠይቀዋል።

https://p.dw.com/p/3f3tJ
Belgien EU-Parlament Angela Merkel
ምስል picture-alliance/AP Photo/F. Seco

የሜርክል ጥሪ

የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል የአውሮጳ ህብረት አባል ሃገራት እንዲተባበሩ ጠየቁ።የወቅቱ የአውሮጳ ህብረት ፕሬዝዳንት፣ ሜርክል ከኮሮና ወረርሽኝ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በተገኙበት በብራሰልሱ የአውሮጳ ህብረት ፓርላማ ባሰሙት ንግግር ህብረቱ አሁን ከጋጠመው ቀውስ ሊወጣ የሚችለው በአንድነትና በመተባበር እንደሆነ አስገንዝበዋል።ሜርክል በብራሰልስ ቆይታቸው አባል ሃገራት ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን በመተው የህብረቱ ያወጣው የ750 ቢሊዮን ዮሮ ከኮቪድ 19 ማገገሚያ እቅድ ተቀብለው እንዲያጸድቁ ጠይቀዋል።የአባል ሃገራት መራህያነ መንግሥታትና ርዕሳነ ብሄራት  በመጪው ሳምንት ብራሰልስ ቤልጅየም ፊት ለፊት ተገናኝተው በሚያካሂዱት ጉባኤ በዚህ ጉዳይ ላይ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ጠቃሚ መሆኑን ሜርክል ትናንት እዚያው ብራሰልስ ካነጋገሯቸው ከህብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርዙላ ፎን ዴርላየንና ሌሎች ሃላፊዎች ጋር ባወጡት መግለጫ አሳስበዋል።የብራሰልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ አለው።
ገበያው ንጉሴ 
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ