1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

ሰኞ፣ ነሐሴ 28 2010

አወዛጋቢዉ የአቶ በረከት ስምዖን ቃለ መልልስ ፤ ዘብጥያ የወረዱት አብዲ ኡመር መሐመድ ፤ የእቴጌ ጣይቱ የክብር ሃውልት ለአዲስ አበባ፤ አርቲስት ታማኝ በየነን ለመቀበል ዝግጅትዋን ያጠናቀቀችዉ ኢትዮጵያ የሰሞንኛዉ የማኅበራዊ መገናኛዉ ዓለም የመወያያ ርዕሶች ናቸዉ።      

https://p.dw.com/p/347kB
Äthiopien Regierungssprecher Bereket Simon zum Tod von Meles Zenawi
ምስል Reuters

«ብአዴን የወሰደዉ ርምጃ ትክክል ነዉ»


መደመር በተግባር"ግድግዳውን ንደን ድልድይ እንገንባ" በሚለው የጠቅላይ ሚንስተራችን የደ/ር አብይ አህመድ መሪ ቃል መሰረት እንሆ የኢትዮ በርሊን ስራ አስኬጅ ኮሚቴ እና የሴቶችና ልጆቾ ንዑሰ ኮሚቴ ተወካዮቾ በበርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቀደም ብሎ ከኤንባሲው በቀረበልን የግንኙነት ግብዣ መሰረት  ነሐሴ 23 ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ተገኝተን ተገኝተን የትውውቅ እንዲሁም በጣም ገንቢና ውጤታማ ውይይት አድርገናል ። ይላል በርሊን ማህበር በፌስ ቡክ ያሰራጨዉ የመደመር ዜና።  ግንኙነቱ በሁለታችንም በኩል የተደሰትንበት ተስፋ የሚሰጥ ኢትዮጵያ ውስጥ በዶ/ር አብይ እና ቲሙ እየተደረገ ያለውን ለውጥ የሚደግፍ ለቀጣይም ግንኙነት መሰረት የሚጥል ሆኖ አግኝተነዋል። በኤምባሲው ተወካዮችም በኩል የኢትዮ - በርሊንን እንቅስቃሴ እንደሚያውቁ እንደሚያደንቁ አና አላማውንም እንደሚደግፉ በአፅንዎት ነግረውን በዚህም ምክንያት ወደፊት ትልልቅ በኀላፊነት የሚሰሩ ስራዎችን አብረውን ለመስራት ፍላጎት አንዳላቸው ገልፀውልን አኛም ፍቃደኛ መሆናችንን ቃላችንን ሰተናል። ይላል ከመዲና በርሊን የተሰማዉ  የመደመር ዜና።  
በያዝነዉ ሳምንት በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የመደመር ዜና ሆኖ በሰፊዉ ሲያወያይ የሰነበተዉ የአንጋፋ ኢትዮጵያዉያን አርቲስቶች ከዓመታት ስደት በኋላ ወደ ሃገራቸዉ መመለስና ሊመለሱ ነዉ ዜና የደስታ ዉይይት ነበር። ከአርቲስቶቹ ጋር የእቴጌ ጣይቱ  ሀውልት በቆረቆሯት አዲስ አበባ ሊቆም መሆኑ ሌላዉ ርእስ ነዉ ። በኢትዮጵያ የቀድሞ የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ ኡመር መሐመድ በቁጥጥር ስር መዋል፤ እና በቅርቡ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ከማዕከላዊ ኮሚቴዉ ያገዳቸዉ አንጋፋዉ የኢሕአዴግ ታጋይና ባለሥልጣን አቶ በረከት ስምዖን ብአዴን  ዶይቼ  ቬለን ጨምሮ ለተለያዩ ብዙሃን መገናኛዎች የሰጥዋቸዉ ቃለ ምልልሶች ማኅበራዊ መገናኛ ተጠቃሚ ኢትዮጵያዉያን የተወያዩባቸዉ ጥያቄና መልስ እያለዋወጠም ነዉ። 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ቡና ለመጠራራት በሚያስችል ርቀት ላይ የሚኖት ጎረቤታቸዉ እማሆይ ድርብ በሚኖሩበት ቤት ዝናብ ሳይበግራቸዉ ቤታቸዉን ለማደስ የመጀመርያዉን ስራ አንድ ብለዉ ማስጀመራቸዉን የሚያሳየዉ ፎቶ በማኅበራዊ መገናኛ በተለቀቀ ፤ ዐብይ አይተኛም እኮ ያሉ የምስጋና አስተያየትን ያስተላለፉ ጥቂቶች አይደሉም። 
«አቶ በለጠ ኃይለጊዮርጊስ የተባሉ የፌስቡk ተከታታይ እንዳሉት፤ መሪ ከንግግር ባለፈ ተግባራዊ ምሳሌ በመሆን ሌሎች ብዙዎችን የበጎ ተግባሩ ተባባረዎችን መፍራትና ተከታ ማብዛት ይችላል። ለሌሎችም ስልጣን ህዝብን ማገልገያ እንጅ የግል መገልገያ እንዳልሆነ፤ ያለፈውን ስርአት መኮነኛ ለሚመጡትም የማስጠንቀቂያ ደውል ነው። ከማነብነብ ባሻገር በተግባር ስላሳየ ብዙ ፍሬ ያፈራል። ዝቅ ብሎ የድሆችን ችግር የሚካፈል መሪ እግዚአብሔር ለኢትዮጵያ ስለሰጠ ስሙ ይባረክ። አንተም ተባረክልን።» ብለዋል 
«የደካማ ሰዎችን ቤት እየወረሱ ለሀብታም እና ለዘመዶቻቸው ከሚያወርሱ መሪዎች ተላቀን የደካሞችን ቤት ወደሚያድሱ መሪዎች ተሸጋግረናል» ሲሉ በፌስቡክ አስተያየታቸዉን ያስቀመጡት ደግሞ ቦኒ ኦሮ ናቸዉ። 
«የተባረከ መሪ ሲሰጥህ የደካሞችን ቤት እንደዚህ ዝቅ ብሎ ይሰራል። የተረገመ መሪ ሲሰጥህ ደግሞ ነብሰጡር በተኛችበት ቤቷን በላይዋ ላይ በዶዘር ያፈርሳል፤ ረጅም ዕድሜና ጤና ለመሪያችን ይስጥልን።» ሲሉ ጆን ላይኩም መርቀዋል። 
በያዝነዉ ሳምንት መጀመርያ ሰኞ ከሰዓት በኋላ የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ።  የፌደራል አቃቤ ህግ አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር የታሰሩት በሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ በብሔር ግጭት፣ በሃይማኖቶች መካከል ግጭት እንዲፈጠር አድርገዋል በሚሉ ወንጀሎች ገለፀ። ከአንድ ቀን በፊት የአቶ አብዲ ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ወስኖ ነበር።  
አባተ ሴዶ የተባሉ የዶይቼ ቬለ ፌስቡክ ተከታታይ  «ተየዙ ብቻ ሰይሆን ለጠፉት ጥፋት ተጣያቅ መሆን አለባቸው። ምንም እንኳ የይቅርታ ዘመን ቢሆንም የሕግ የበላይነት መከበር አለባት። ተገቢ ቅጣት መግኘት አለበት።» ብለዋል 
« አብድ ኢሌ ከወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ነዉ እንዴ? ሲሉ አስተያየታቸዉን በጥያቄ የሚጀምሩት ደግሞ ዙ ማ የተባሉ የዶይቼ ቬሌ ፊስ ቡክ ተከታታይ ናቸዉ።  ከወደ ትግራይ ጫጫታ ባዛ ቀኝ እጃቸው ተቆረጠ። የኮትረባን መንገዱ ተዘጋ ያሶማሌ ክልል ባጀት ለልማት ነዉ የወያኔ ጀኔራሎች መምጠጫ ቱቦ ተቋረጠ።» 
በኦሮምያ ሰው ተዘቅዝቆ ሲገደል ሌሎች በተለያየ ምክንያት ሲገደሉ ለምን ለማ ኣለተጠየቀም ፣በአማራ ክልል የትግራይ ተወላጆች ሲጨፈጨፍ ለምን ገዱ ና ደመቀ ኣልተጠየቁም። ይህ ሰብኣዊና ዲሞክራስያዊ መብት ጥስት ኣይደለም እንዴ? ሲሉ የሚጠይቁት ደግሞ ተመስገን አምላኬ የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ ናቸዉ። 
ዳናት ወንደሰን ብርሃኔ በበኩላቸዉ ሁሌ ፋሲካ የለም ።ዛሬ ሌላ ደሞ ቀን ነው። ቂሊንጦ እስር ቤት እልል ብላ ትቀበልሃለች። ትክክለኛውን ፍርድ ደግሞ ከሞት ባሻገር ጠብቅ። የማርያምን የእግዚአብሔርን ምሕረትና ጭካኔን ታይበታለህ። ምሕረቱን በምድር ላይ ሳለህ ፀፀቱ እንደ እግር እሳት አቃጥሎህና ተሰምቶህ ከተመለስህ ነው። ለዚህም ነው ዕድሜን ለንስሃ የቀጠለልህ። ጭካኔውን ደግሞ በምድር ላይ የተሰጠህን የንስሃ ጊዜ ካልተጠቀምክበት በላይኛው ቤት የእግዚአብሔርን ጭካኔ ታይበታለህ። ጩኸትህ ግን ከንቱ ነው። እሪ ብለህ ያዙኝ ልቀቁኝ ብትል ሕወሃት ሊያድንህ አይችልም።

Emblem der Tigray People's Libration Font (TPLF)
Deutschland | Junge Frau mit Fliegenklatsche in Berlin
ምስል imago/Steinach

ብራቮ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን!! ሲሉ አስተያየታቸዉን የፃፉት አቶ ቲፊክ አብደላ የመብት ተሟጋቹ ድርጅቱ ከአቶ አብዲ መሐመድ ኡመር በተጨማሪ የክልሉን ባለሥልጣናት የደገፉ፤ ልዩ ፖሊስ የሚባለዉን ኃይል ያደራጁ፤ ያስታጠቁ እና የሠብአዊ መብት ጥሰቱን ለረጅም ጊዜ በቸልታ ያለፉ የፌደራል መንግሥት ባለሥልጣናት እና ሌሎች አካላትም ሊጠየቁ ይገባል የፍትህ ግማሽ የለዉም!! ከፌደራል ጀምሮ ያሉ አካላት እንደ ጥፋት ደረጃቸዉ ካልተጠየቁ አንድ ግለሰብ ማሰሩ ብቻዉን ህዝብን ማታለል ነዉ!!! ብለዋል። 
ብዙወሬ በአህያ አይጫንም እና የሰዎቹ የምርምራ መዝግብ እንደተጠናቀቀ (ሄግ ኔዘርላንድ)ወደ የሚገኘው የዓለም አቀፍ የጦር ወንጀለኞች ተመልካች ፍርደ ቤት ክሳቸወን እንዲላክልን እንጠይቃልን ሲሉ አና ፋራህ አስተያየታቸዉን ይደመድማሉ።  
አቶ አለምሰገድ የተባሉ የዶይቼ ቬለ ተከታታይ ለማንኛዉም "የአትላሱን" የአብዲ ኢሌ ቤት ባትጋሩኝ ሲሉ ጠይቀዋል። አቶ ዮሴፍ ይታና በበኩላቸዉ «መንግስታችን ሆይ አትቆጥብ ማገዶ ፤ በነካ እጅህ ቀጥል ከተከዜ ማዶ !!!»  ሲሉ ተቀኝተዋል። 
ጀምበር ምነው ገባች...በጊዜ ተሸባ፤ ብላችሁ አትበሉ ... ጥበብ ስታነባ፤  ሌላ ጣይ ይወጣል ... ፀሀይ ስትገባ ። ምህረት ከበደ የተባሉ የፊስቡክ ተከታታይ የጥበብ እመቤትዋ አዲስ አበባ መግባትዋን ሲያዩ የቋጠሩላት ስንኝ ነች። በሳምንቱ መጀመርያ አርቲስት ዓለምፀሐይ ወዳጆን ጨምሮ አራት አንጋፋ የጥበብ ጻለሞያዎች አዲስ አበባ ሲደርሱ  ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ገላቸዉ።  ብሔራዊ ትያትር ከተካሄደዉ የአቀባበል ሥነ-ስርዓት በኋላ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ወደ ሀገራቸው የተመለሱትን አርቲስት ዓለምፀሓይ ወዳጆ፤ አርቲስት አበበ በለው እና አርቲስት ተክሌ ደስታን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።   አርቲስት ዓለም ፀሐይ ወዳጆ የእቴጌ ጣይቱ  ሀውልት በቆረቆሯት አዲስ አበባ ለማቆም የመሰረት ድንጋይ መጣሉን የሰሙ ኢትዮጵያዉያን ደስታቸዉን አካፍለዋል።  አርቲስት 
ዓለምጸሐይ ወዳጆ የተናገረችዉን አካፍለዋል።  ቀደም ሲል የሚዲያ ሽፋን እንዲሰጥ ስለመጠየቅ በሚል የተሰራጨዉና የአዲስ አበባ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ አርማ ያለበት መጥርያ እንደሚያሳየዉ « የአዲስ አበባ መስራች ለነበሩት ለእቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ የመታሰብያ ሀዉልት ለማቆም የመሰረት ድንጋይ ይቀመጣል። የመሰረት ድንጋዩ የሚቀመጠዉ በአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ በክቡር ኢንጂኔር ታከለ ኡማ እና በተወዳጅዋ አርቲስት ዓለምፀሐይ ወዳጆ ነዉ።  የመሰረት ድንጋዩ ነሐሴ 24 2010 ዓ,ም ከቀኑ 7: 30 አድዋ ድልድi አካባቢ በሚገኘዉ ሲግናል አደባባይ መሆኑን ነበር።    
በምክትል ከንቲባ ታከለ ዑማ « በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተሰራጨዉ መረጃ ሁሉ እንደ እዉነት ከተወሰደ አስቸጋሪ ሁኔታን ይፈጥራል» ሲሉ በፊስቡክ ገፃቸዉ መልክታቸዉን ዉን አስተላልፈዋል። 
ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ዛሬ በድጋሚ ለእቴጌ ጣይቱ ሀውልት የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ ስርዐትን በተመለከተ የተሰራጨው ደብዳቤ ከእሳቸው ቢሮ አለመውጣቱን ተቃውሞ ላሰሙ ሰዎች መናገራቸዉም በዚሁ በማኅበራዊ መገናኛዎች በብዛት የተሰራጨ መረጃ ነዉ። ጫና የበረታባቸው ምክትል ከንቲባ ታከለ ከከተማው ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊዎች ጋር በመሆን ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጡ ይሆን? ማኅበራዊ መገናኛ ተጠቃሚ ኢትዮጵያዉያን ተስፋቸዉን አክለዉ አስቀምጠዋል።
በመንግሥት ቤት እንደሚኖሩና ምንም አይነት ንብረት እንደሌላቸዉ ሃገራቸዉን በትጋት እንዳገለገሉ በተለያየ የብዙሃን መገናኛ እየቀረቡ መናገር የጀመሩትና አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ከማዕከላዊ ኮሚቴዉ ያገዳቸዉ አንጋፋዉ የኢሕአዴግ ታጋይና ባለሥልጣን አቶ በረከት ስምዖን በሚሰጥዋቸዉ ቃለ ምልልሶች በማኅበራዊ መገናኛ ብዙ ጥያቄዎችን እያጫሩ ነዉ። እሳቸዉ እንደሚሉት ዝም ብዬ ብቀመጥም የብአዴን ባለሥልጣናት ጉትጎታ እዉነቱን እንድናገር አስገድዶኛል፤ የሚቆሰቁሱን እነሱ ናቸዉ። 
ለበርካታ ጋዜጠኞች መሰደድ፤ በሃገሪቱ የፕሬስ ነፃነትን በማፈን፤ በአሸባሪነት ሰዎችን በማሳሰር እና በማሰቃየት በረከት ስምኦን በበርካታ ኢትዮጵያዉያን ይከሰሳሉ ትችት ይቀርብባቸዋል።  የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ  ቴሌቭዝን ዋና ተጠሪ አቶ ጃዋር መሐመድ ለአቶ በረከት መልስ ሰጥተዋል። አዎ በሃገሪቱ ለዉጥ እንዲመጣ ጥረዋል ግን በሌላ መንገድ። « በረከት ማለት ብአዴን የወያኔ አሽከር አድርጎ ሲኡeከረክራት የነበረ ነዉ። አዎ በረከት ለዉጥ እንዲመጣ ፈልጎአል። ግን አምባገነናዊ ስርአትን የሚያራዝም ዘገምተኛ የጥገና ለዉጥ ነበር ሲያካሂድ የነበረዉ።»
አቶ በረከት የቀድሞዉ ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደስአለኝ በስልጣን ጊዜያቸዉ ሃገሪቱን መምራት ያልቻሉ በወያኔ ጫና ነዉ መባሉን ማጣጣላቸዉ ሌላዉ ማኅበራዊ መገናኛን አጀብ ያሰኘ ነዉ። 
«አቶ ኃይለማርያም የራሱ ድክመት ነዉ። በኅገመንግሥት የሚመራ ስልጣን ይዞ ስልጣን አልነበረኝም የሚልሰዉ ሕገ መንግሥቱን አያዉቀዉም። ኢትዮጵያ በዚህ ሰዉ መመራትዋ በጣም ያሳዝናል።» 
አቶ ጃዋር በበኩላቸዉ እኔ በረከት ስምኦን ብሆን ኖሮ እደበቃለሁ›› ብአዴን አቶ በረከት ላይ የወሰደዉን ርምጃ ትክክል ነዉ፤ ሃሳብን የማንሸራሸር ጅማሮዉም ይበል የሚነኝ ነዉ ። 
«የፕሬስ ነጻነትን ያቀጨጨዉና ያፈነዉ በረከት ስምኦን ነዉ። እንደሱ አይነe ሰዎች በፍጥነት ራሳቸዉን መለወጥ ካልቻሉ፤ መንጭቆ መጣል አስፈላጊ ነበር ብአዴን የወሰደዉ ርምጃ ትክክል ነዉ።»  
ብአዴን ከበረከት ስምኦን ጋር ከማዕከላዊ ኮሚቴዉ ያገዳቸዉ አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ)  ዝምታን መርጠው ቢቆዩም በደብዳቤም ሆነ ብዙሃን መገናኛ ጋር በመቅረብ በገዛ ፍቃዳቸዉ መልቀቃቸዉን እየተናገሩ ነዉ። ማኅበራዊ ሚዲያዉ አሁን ከቅዳሜ ማለዳ ጀምሮ አርቲስት ታማn በየነን አዲስ አበባ ፤ ሸገር ፤  በረራ፤ ፊንፊኔ ላይ እየጠበቀ ነዉ ፤ ታማኝ እና ኢትዮጵያ አሸነፉ! ብሩክ ይባስ በፊስ ቡክ ድረገፁ ።ታማኝ በሀገሩ ጉዳይ ሳይደራደር የህወሀት ጀንበር ዳግም ላትወጣ ጠልቃለች ። እናም ዛሬ ሀገሩን እያለ ወደ ሀገሩ እያመራ ነው። የሀገሬ ህዝብ ሆይ ታማኝን አደራ። መውጣት መግባቱ የእናንተ ነው። እሱ እንደታመነ ሀገሬን እንዳለ ካዘኑት ጋር እያዘነ ከሚያልቅሱት ጋር እያለቀሰ በደስታም እየተካፈለ ዛሬ ላይ ደረሰ ።እነሆ ከ22 ዓመታት ስደት በኋላ ወደ ውድ ሀገሩ ሊመለስ ሆነ አምላክ ይመስገን። 
ሙሉ ስርጭቱን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ! 

Amhara National Democratic Movement (ANDM) logoAmhara National Democratic Movement (ANDM) Logo von Amhara National Democratic Movement ANDM
ምስል ANDM centeral Comittee office
Flash-Galerie Der Blick aus meinem Fenster Addis Abeba Äthiopien
ምስል S. Mengist


አዜብ ታደሰ 


አርያም ተክሌ