የማረቆ ብሄር ተወላጆች የተቃውሞ ሰልፍ በሐዋሳ
ሐሙስ፣ መጋቢት 29 2014ማስታወቂያ
በጉራጌ ዞን የማረቆ ብሄር ተወላጆች ቀደም ሲል ያቀረብነው የልዩ ወረዳ መዋቅር እና የማካለል ጥያቄ ተግባራዊ ይደረግልን ሲሉ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ባካሄዱት ሠላማዊ ሠልፍ ጠየቁ። ከሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ አቶ ሞሣ ዋቤቶ የሰልፉ አላማ የማረቆ ሕዝብ እራሱን በቻለ ልዩ ወረዳ እንዲደራጅ እና ከመስቃን ወረዳ ጋር የሚያዋስኑት 9 ቀበሌያት በሕጋዊ መንገድ እንዲካለሉ ለመጠየቅ ሲሉ ለዶቼ ቬል (DW) ተናግረዋል። ዝርዝሩን የሀዋሳው ወኪላችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ልኮልናል።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ