1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

ዓርብ፣ ሚያዝያ 14 2014

ስሞኑ በማሕበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች ትኩረትን ስበው ከነበሩት መካከል የ12ኛ ከፍል ፈተናና የትምህርት ሚኒትቴር ውሳኔዎች፣ ለሩሲያ "መዋጋት እንፈልጋለን" ያሉ ኢትዮጵያውያን በሩስያ ኤምባሲ መኮልኮል እንዲሁም የሰሜን ሽዋው ግጭት ይገኙበታል። 

https://p.dw.com/p/4AIrK
Social Media Apps | WhatsApp Facebook Twitter Instagram
ምስል Nasir Kachroo/ZUMA Press/imago images

የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና እርማት እና ውጤትን አስመልክቶ ትምህርት ሚኒስቴር በሰጠው  መግለጫ  ፈተናውን በሁለት ዙር ከወሰዱ ከ598ሺ በላይ ተማሪዎች መካከልም 45 % ያህሉ  ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያስገባቸውን ውጤት አግኝተዋል። ይሁንና የመንግሥት ዩንቨርስቲዎች የቅበላ አቅም  ከተፈተኑት ተማሪዎች  25% ያህሉን ብቻ መሆኑም አሳውቋል። 
በተጨማሪም ባለፈው ዓመት በጦርነት እና ግጭት ቀጣና ውስጥ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ወስደው ማለፍ ያልቻሉ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በ2014 ዓ.ም እንደ መደበኛ ተማሪ መፈተን ይችላሉ ሲል ወስኗል።
አቶ ውርቁ በዳዳ የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ተከታዩን አስተያየት ሰንዝሯል "በመጀመሪያ ደረጃ ፈተና ማለፍ ማለት አማካይ( 50%) ማምጣት አይደለም። አቅሙን አውቆ ማለፊያ ነጥብ ማስቀመጥ ያለበት ራሱ ትምህርት ሚንስቴር መሆን አለበት።60% ወይንም 75% ብሎ ማስቀመጥ ይችላል። በሁለተኛ ደረጃ የቅበላ አቅም ነው ወይስ እጩ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ስታንዳርድ ያሟላሉ የሚለው ነው የሚታየው። ለኔ ስታንዳርድ መኖር አለበት። ሁሉንም ተፈታኝ ተማሪዎች (ያለፉትን አላልኩም) የመቀበል አቅም ያላቸው ዩኒቨርሲቲዎች ቢኖሩን ሁሉንም እናስገባለን ማለት አይደለም። እኔ የቅበላ አቅም የሚለውን አልወደውም! መታየት ያለበት የተማሪ አቅም ነው።
ትምህርት ሚንስቴር 45% አልፈዋል ብሎ ካመነ ግን ሁሉም ዩኒቨርሲቲ መግባት አለባቸው። ዶርም/ሆቴል/ኮንዶሚንዬም ተከራይቶላቸው በሺፍትም ቢሆን ይማሩ። ወይ ጎረቤት ሀገር ተመቻችቶላቸው ይማሩ።በትውልድ መቀለድ የለብንም"
 ደምለው አስፋው የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይም አዘር ያለች አስተያየት ሰንዝሯል

"ሌብነቱን ይፋ በማድረግ በትክክል መሰረቁን ለህዝብ ይፋ ማውጣት ወይስ ባለተረኞቹን ፈርቶ ማድበስበስና ሕዝብን መካድ:"


አቡ ፉአዝም እንዲሁ በፌስቡክ 
"ሌላ ሀገር ቢሆን ትምህርት ሚኒስትሩ በህግ ይጠየቁ አሊያም ከስልጣን ይባረሩ ነበር።"
በማለት አስተያየታቸውን አስቀምጧል።

Facebook
ምስል Richard Drew/AP/picture alliance

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በኤፍራታ ግድም ወረዳ በተቀሰቀሰ ግጭት በርካቶች ለሞት መፈአልና መፈናቀል እንዲሁም ለንብረት መውደም ምክንያት ሆኗል። DW ይህን ዜና "በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በኤፍራታ ግድም ወረዳ እና በአካባቢው ግጭት መቀስቀሱን የአይን እማኞች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች እና ባለሥልጣናት እንደሚሉት ችግሩ ከተፈጠረበት ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ የሚደረግ የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጧል።" ሲል ዘመዘገቡ ይታወሳል።  ሰይድ ዳውድ የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ
 "ግጭት ? የመኪና ነው ? የሆነውን ግጭት የሚለው ቃል ይገልጸዋል ?"
በማለት በጥያቄ ጀምረው በጥያቄ በመጨረስ DWን ይወቅሳሉ።

"መንግስት የለም ማለት ነዉ"
አሉ። ስንታዮህ ከበደ የተባሉአስተያየት ሰጪ"መንግስት የማያውቀው ምንም ነገር የለም፣እርምጃ ለመውስድ እጁን ለምን እንደ ሰበሰበአላውቅም፣ግን እስከመቼ እዛ አካባቢ"በማለት አስተያየታቸውን ገልጸዋል። 
MI የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚም

"መንግስት የህዝብን ደህንነት እስካላስጠበቀ ድረስ አለ ማለት ያስቸግራል።በተደጋጋሚ እዚህ አካባቢ ያለውን የሚታወቅ የሽፍታ ቡድንን ለምን ማጥፋት አልተቻለም? ምናልባት ሽፍታው እንዳይጠፋ የመንግስት ተብዬው ፍላጎት ሳይሆን አይቀርም!"
በግጭቱ ዙሪያ በርካታ ዘለፋ አዘል አስተያዬቶችም ጭምር ተሰንዝሯል። በአንጻሩም 
"በአሁኑ ሰአት ከደሴ አዲስ አበባ የሚወስደው የፌደራል መንገድ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል"
ብሏል አሰገደው ወሰኔ በፌስቡክ። መሐመድ አህመድም 

"ተፈጥሮ በነበረው የአካባቢ ግጪት ትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡ ይታወቃል። በአሁን ሰኣት አካባቢው ሰላም በመሆኑ አልሀምዱ ሊላህ መንገዱ ተከፍቶ መኪኖችእንቅስቃሴ ጀምረዋል።" ብለዋል።
የሩስያና ዩክሬይን ጦርነት ለኢትዮጵያውያን ዳፋው በዘይትና በስንዴ የሚያልቅ አይመስልም ። ሩስያ አዲስአበባ በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩል ወዶ ዘማች ወጣቶች ለመመልመል የቅጥር ማስታወቂያ አውጥታለች ተብሎ ከተነገረበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ የአዲስ አበባና አካባቢዋ ነዋሪዎች በሩስያ ኤምባሲ ተሰልፈው ታይቷል። ሁለቱም አገሮች በሚያመርቱት የጦር መሳሪያ አገር ውስጥ ያለው መተላለቅ አልበቃ ብሎ ልጆቻችን ለምልመላ መጋበዛቸው ትክክል አደለም የሚል በአንድ ወገን የለም መዝመታቸው ትክክል ነው የሚልም በሌላ ወገን ሆነው በርካታ ክርክሮች ተካሂዷል። በዚህ ርእሰጉዳይም ከተሰጡ አስተያየቶች የተወሰኑትን እናስደምጣችሁ።

አየር ጤና በሚል ስያሜ የሚታወቁ ሌላው አስተያየት ሰጪ ድል ለሩስያ ብለዋል
"ለሩስያ መዋጋት የኑሮ ውድነትን ፍራቻ ሳይሆን የአሜሪካንና የምዕራባውያንን ሴራ ከሩስያ ጋር በትብብር ለመውጋትና የምዕራባውያንን ኢፍትሀዊ አስራርን ከስሩ ቆርጠን ለመጣል ነው
ድል ለሩሲያ" አበበ ዘውዱም ለሩስያ ወግነን መዋጋታችን ስለምእራባውያኑ ክፋት ብለን ነው ይላሉ 

"በኑሮ ውድነቱና ዩክሬንን በመጥላት ሳይሆን ሩስያ ለሃገራችን ህልውና ከታሪክ እስከዛሬ መፍረሳችንን ከሚፈልጉና ከሞከሩ አንዳንድ ምዕራባውያን ሃገራት በተቃራኒ በመቆም ላሳየችን የውለታዋ ምላሽ ነው። በፀሎትና አቅማችን በፈቀደው ሁሉ ለሩስያ ድልን እንመኛለን። ስለ ምዕራባውያን ክፋት ስንል ነው ምክንያታችን።"

ሞገስ አዱኛ የወጣቱን ለሩስያ ተሰልፎ ለመዋጋት ያሳየው ፍላጎት ዲፕሎማሲያዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶችን እንዲህ ሲሉ ይዘረዝራሉ

"እኔ እንደሚመስለኝ የራሺያ መንግስ ኢትዮጵያ ላይ የተከተለው ፐብሊክ ዲፕሎማሲ የኢትዮጵያውያንን ልብ አሸፍቷል በተለይ ራሽያ በተባበሩት መንግስታት በሚደረጉ የሰባዊ መብት ጥሰት ውግዘቶችን በመቃወም ኢትዮጵያን በመደገፏ ምዕራባውያን በተለይም የአሜሪካ ሴኔትና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኢትዮጵያን ለመቅጣት የሚያወጧቸውን ሪዞሊዩሽኖች የራሽያ ፌደሬሽን በጥብቅ መቃወሟ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ የፐብሊክና የፓለቲካል ዲፕሎማሲ ተቀባይነት አስገኝቶላታል። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያን ለመበታተን የሚሰሩትን ምዕራባውያን በራሽያ ፎዴሬሽን መከላከያ ተቋሞች ገብተው መበቀል ይፈልጋሉ። ከዚህም ባለፈ ጣራ የነካውን የኑሮ ውድነት ለማምለጥና ወደ አውሮፓ ለመግባትና የተሻለ ህይወት ለመምራት አብዛኛው ወጣት መዝመቱን ፈልጎታል።"
"አይ ትውልድ የራሷ ሲያርባት የሰው ታማስላለች"

አለም ብርሃን።

"ውይ ሐበሻ በቃ እንዲህ ውርደት ቀለባችን ይሁን"
መህረት ሃይሉ
መላኩ በንቲ የተባሉም እንደ አለም ብርሃን ሁሉ የራሷ አሮባት በሚል ጀምረው "የራሷ አሮበት የሰዉን ታማስላለች አሉ ለኢትዮጵያ ተዋጉ መጀመሪያ ለነገሩ ድህነት ለመሽሽ ይመስለኛል እንጅ ለውግያ አይመስለኝም"
ዮሃንስ ግረሱ "የራሱን ልጅ አስከሬን አዝሎ የታመመውን የሹም ልጅ ለመጠየቅ ይሄዳል ነዉ ነገሩ። ያሳዝናል!"

ወይ ጉድ ብሎ ይከምራል የሃብቶም AR አስተያየት። "ወይ ጉድ! አየ ጦቢያዊያን ሳልኩት እኩ አሜሪካ የቅጥር ማስታወቂያ ብታወጣ የጦቢያ ሚኒስትርሩ፤ ሼኩ ፤ ጳጳሱ፤ የተማረ ያልተማራ፤ ኢታማዦር ሹሙ በሙሉ ሰልፍ ይይዙ ነበር።  አሜሪካ ለመሄድ ስለት እያስገባ የሚፀልየው ሰው እዚህ ይመጣና አሜሪካ ተንከሲስ የሆነች ሀገር ይላል"
በዚሁ የሃብቶም AR አስተያየት የዛሬው ዝግጅት ፈጸምን።

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር 

እሸቴ በቀለ