1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማሊ ወታደራዊ አስተዳደር የሲቪል መሪ ስያሜ ቀነ ገደብ

ማክሰኞ፣ መስከረም 5 2013

የማሊ ወታደራዊ አስተዳደር ጊዜያዊ የሲቪል መሪ የሚሰየምበትን ቀነ ገደብ ሊወስን ነው። ወታደራዊ ቡድኑ ቀነ ገደቡን ለመወሰን ማሊ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ አዲስ ምርጫ እንድታደርግ  አጥብቀው ከሚሹ  የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ በምህጻሩ ኢኮዋስ አባል ሀገራት መሪዎች ጋር ጋና አክራ ውስጥ ዛሬ ውይይት ጀምሯል።

https://p.dw.com/p/3iVjv
Mali CNSP Gespräche Putsch Malick Diaw ssa Kaou Djim
ምስል Getty Images/AFP/M. Cattani

የማሊ ወታደራዊ አስተዳደር ጊዜያዊ የሲቪል መሪ የሚሰየምበትን ቀነ ገደብ ሊወስን ነው። ወታደራዊ ቡድኑ ቀነ ገደቡን ለመወሰን ማሊ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ አዲስ ምርጫ እንድታደርግ  አጥብቀው ከሚሹ  የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ በምህጻሩ ኢኮዋስ አባል ሀገራት መሪዎች ጋር ጋና አክራ ውስጥ ዛሬ ውይይት ጀምሯል። ባለፈው ነሐሴ ወር የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡበከር ኬይታን አስወግዶ ስልጣኑን የተቆጣጠረው የወታደራዊው አስተዳደር ለቀጣዮቹ ሶስት አመታት በስልጣን ላይ ለመቆየት ማቀዱን ካስታወቀ በኋላ በተለይ ከቀጣናው ሃገራት ብርቱ ተቃውሞ ደርሶበት ነበር። ነገር ግን ወታደራዊው ቡድን በተለይ ከቀጣናው ሃገራት በደረሰበት ብርቱ ተቃውሞ  በአንድ አመት ከስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ምርጫ እንዲደረግ ፍላጎቱን አሳይቷል።  ዘጠኝ የቀጣናው ሀገራትን ያሳተፈ ስብሰባ ጋና አክራ ውስጥ ከማሊ ወታደራዊ አስተዳደር ጋር ዛሬ ሲያገናኝ የሲቪል የሽግግር መንግስት መሪ የሚሰየምበትን ቀነ ገደብ እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል። በተጨማሪም  በማሊ የሚዋቀረው አዲሱ የሲቭል የሽግግር መንግስት መሪ ከየት ይሰየም የሚለው አጀንዳ ከአንዳች ስምምነት እንዲደረስ በብዙዎች ዘንድ እየተጠበቀ መሆኑን  የአሶሽየትድ ፕረስ ዘግቧል። ወታደራዊ ቡድኑ የሽግግር መንግስት መሪው ከወታደሩ ይሰየም ሲል ኢኮዋስ በበኩሉ መሪው ከሲቭል እንዲሰየም ብርቱ ፍላጎት አለው። 

ታምራት ዲንሳ 

አዜብ ታደሰ