የመጨረሻው ሽኝት በአዲስ አበባ
ማክሰኞ፣ ሰኔ 18 2011ማስታወቂያ
በመጨረሻው የክብር ስንብት ላይ የኢፌድሪ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል። በስነሥርዓቱ ወቅትም የሁለቱም የጦር ጀነራሎች የሕይወት ታሪክ የተነበበ ሲሆን፤ በቅርበት የሚያውቋቸው ባልደረቦቻቸው እና ጓደኞቻቸው ታሪካቸውን ለታደሙት በማካፈል በህልፈታቸው ቁጭት ሀዘናቸውን ገልጸዋል። ልጆቻቸውን እንዲሁም የሃይማኖት አባቶችም የየበኩላቸውን መልእክት አስተላልፈዋል። በስፍራው ተገኝቶ የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ያጠናቀረውን ልኮልናል።
ሰሎሞን ሙጬ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ