1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የመጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅት

ሰኞ፣ መጋቢት 7 2018

በአትሌቲክስ ኢትዮጵያዉያን አትሌቶች በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት በተለያየ የዓለም ክፍል ታላላቅ ድሎች የተጎናጸፉባቸው ዉጤቶች ተመዝግበዋል። የኢትዮጵያ ታሌቲክስ ብሄራዊ ቡድን ፖላንድ በምታስተናግደው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ላይ የመሳተፉ ነገር ገና ርግጥ አልሆነም።

https://p.dw.com/p/5AUir
ፎቴን ተስፋይ የበርሊንን ግማሽ ማራቶን እጎበ በ 2025 ስታሸንፍ
ፎቴን ተስፋይ የበርሊንን ግማሽ ማራቶን እጎበ በ 2025 ስታሸንፍምስል፦ Jörg Carstensen/dpa/picture alliance

የመጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅት

  
በአትሌቲክስ ኢትዮጵያዉያን አትሌቶች በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት በተለያየ የዓለም ክፍል ታላላቅ ድሎች የተጎናጸፉባቸው ዉጤቶች ተመዝግበዋል። የኢትዮጵያ ታሌቲክስ ብሄራዊ ቡድን የፊታችን ዐርብ ፖላንድ ከምታስተናግደው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ላይ የመሳተፉ ነገር ገና ርግጥ አልሆነም። በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ፤ ላሊጋ እና ቡንደስ ሊጋ በሳምምቱ መጨረሻ ቀናት ዉጤት እና ትኩረት የሳቡ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ ። የቻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ለመግባት የሚደረገው ትንቅንቅ ከነገ ማክሰኞ ጀምሮ የሁለተኛ ዙር ጫወታዎች ይደረጋሉ ፤ ተጠባቂ ጫወታዎቹን እናነሳለን። 

አትሌቲክስ  


ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በስፔን ባርሴሎና እና በደቡብ ኮሪያ ሴዑል የተካሔዱ የማራቶን የሩጫ ውድድሮችን አሸነፉ። ኢትዮጵያዊቷ ፎቴን ተስፋይ በባርሴሎና የተካሔደውን ውድድር በ2 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ከ53 ማይክሮ ሰከንድ በማጠናቀቅ አሸንፋለች። የ28 ዓመቷ ፎቴን ውድድሩን ያጠናቀቀችበት ጊዜ በታሪክ የዓለም ሁለተኛው ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል። 
በውድድሩ የዓለም ክብረ ወሰን የማሻሻል ዕቅድ እንደነበራት የገለጸችው ፎቴን በገጠማት ከባድ ንፋስ ሳቢያ የውድድሩን መጨረሻ በፈለገችው ፍጥነት መግፋት እንዳስቸገራት ገልጻለች። ይሁንና በሚቀጥለው ማራቶን ክብረ ወሰን ለማሻሻል ዓላማ እንዳላት ከውድድሩ በኋላ ፎቴን ተናግራለች። 
ፎቴንን በመከተል ዩጋንዳዊቷ ጄፕኮይጌይ ኪፕሊሞ ሁለተኛ፤ ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ዘይነባ ይመር ሦስተኛ ወጥተዋል። 
በደቡብ ኮሪያ ዋና ከተማ ሴዑል በተካሔደ ተመሳሳይ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ በአሸናፊነት አጠናቀዋል። በሴቶች ሔቨን ኃይሉ በ2 ሰዓት ከ19 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ ውድድሩን ስታጠናቅቅ በቀለች ጉደታ በ30 ሰከንዶች ዘግይታ ሁለተኛ ወጥታለች። ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ቦሰና ሙላቴ ሦስተኛ ሆና ውድድሩን ጨርሳለች። 
በወንዶች ሐፍቱ ተክሉ በ2 ሰዓት ከ04 ደቂቃ ከ23 ሰከንዶች በመጨረስ ሲያሸንፍ፤ ጌታነህ ሞላ በሁለት ሰከንዶች ብቻ ዘግይቶ ሦስተኛ ጸጋዬ ታደሰ አራተኛ ሆነው አጠናቀዋል። 
ከአትሌቲክስ ዜና ሳንወጣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን የፊታችን ዓርብ ፖላንድ ውስጥ በሚጀምረው የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ለመሳተፍ የሚያስችለውን ቪዛ እስካሁን አለማግኘቱ አነጋጋሪነት መቀጠሉን የሚመለከት መረጃ ይዘናል። 
የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር የፊታችን አርብ ኩጃዊ ፖላንድ ውስጥ ቢደረግም የአሸናፊነት ቅድመ ግምት የተሰጣቸውን ጨምሮ በርካታ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን አባላት የፖላንድ ቪዛ ማግኘት አልቻሉም። ይህን ዘገባ እስካጠ,ናቀርንበት ሰዓት ድረስ አሰልጣኞችን ጨምሮ ታዋቂ አትሌቶች በውድድሩ የመሳተፍ ዕድላቸው መጥበቡ እየተሰማ ነው ። 

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን እስካሁን ቪዛ አላገኘም
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን እስካሁን ቪዛ አላገኘምምስል፦ Haimanot Turuneh/DW

እግር ኳስ 


ፕሪምየር ሊግ 
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በሳምምቱ የመጨረሻ ቀናት ከተከናወኑ አበይት ውድድሮች መካከል የሊጉ መሪ አርሰናል ኤቨርተንን 2 ለ 0 በማሸነፍ መሪነቱን ወደ 9 ነጥብ ያሰፋበት አጋጣሚ ተጠቃሽ ነው። በጫወታው አርሴናል ነጥብ ጥሎ ሊወጣ ጫፍ በደረሰበት አጋጣሚ ተቀይሮ በመግባት ክለቡን በመታደግ ለራሱም አዲስ ታሪክ የጻፈው ዕለቱ ኮከብ ደግሞ የ16 ዓመቱ ወጣት ማክስ ዶውማን ዋነኛው መነጋገሪያ ነው። ታዳጊው ተቀይሮ ከገባ በኋላ በፈጠረው ጫና ለቪክቶር ጂዮክሬስ ግብ እንዲሆን ኳስ አመቻችቶ በማቃበል የቀጥታ የጎል ተሳትፎ ሲያደርግ  በራሱ ጥረት ያስቆጠረው ግብ ደግሞ በፕሪምየር ሊጉ ታሪክ 'በጣም ትንሹ ግብ አስቆጣሪ' የሚለውን ክብረ ወሰን የግሉ አድርጓል።  በሌላ በኩል የማንቸስተር ሲቲ ጉዞ መንገዳገድ ውስጥ መግባቱ ለሊጉ መሪ ምቾት ፈጥሮለታል። ሲቲ ወደ ለንደን ተጉዞ ከዌስትሃም ጋር ባደረገው ጫወታ 1 ለ 1 አቻ  በመለያየቱ ፔፕ ጋርዲዮላን ከባድ ፈተና ውስጥ ጥሏቸዋል።

የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ
ቲ ወደ ለንደን ተጉዞ ከዌስትሃም ጋር ባደረገው ጫወታ 1 ለ 1 አቻ  በመለያየቱ ፔፕ ጋርዲዮላን ከባድ ፈተና ውስጥ ጥሏቸዋል።ምስል፦ Matt West/Shutterstock/IMAGO

የቀድሞ የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ፣ የሊቨርፑል እና የሪያል ማድሪድ አጠቂ ማይክል ኦዌን 'የዋንጫው ፉክክር አብቅቶለታል' ሲል ተደምጧል።
በሊጉ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት  ፉክክሩ  ለዋንጫ ብቻ የተደረገ አልነበረም።  የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ለማግኘት የሚደረገው ትግልም እጅግ ተፋፍሟል። ማንቸስተር ዩናይትድ አስቶን ቪላን 3 ለ 1 በማሸነፍ በ3ኛ ደረጃ ላይ በምቾት መቀመጥ ያስቻለውን ዉጤት አስመዝግቧል። ባለፈው ክረምት አሰልጣኙንና አንበሉን ያጣው ብሬንትፎርድ በ7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ወደ አውሮፓ መድረክ ለመግባት እያለመ መሆኑ ደግሞ እንደ ትልቅ ተአምር ታይቷል።" ሊቨርፑል ትናንት ምሽት ላለመውረድ የሚታገለውን ቶተንሃምን አስተናግዶ አንድ   አቻ በመለያየቱ ወደ አራተኛ ከፍ ሊል የሚችልበትን ዕድል አምክኗል። 

 

ላሊጋ 


"በአውሮጳ አህጉር በሚደረጉ የእግር ኳስ ግጥሚያዎች አሁን አሁን 'አስገራሚ' ነገሮች እየተለመዱ መጥተዋል። በሳምምንቱ የመቸረሻ ቀናት በበላ ሊጋ ከተደረጉ ወሳኝ ግጥሚያዎች መካከል የሪያል ማድሪዱ አርዳ ጉለር ዓለምን ጉድ ያሰኘበት አጋጣሚ አንዱ ነው። ባለፈው ቅዳሜ ሪያል ማድሪድ ከኤልቼ ጋር በነበረው ጨዋታ ቱርካዊው ኢንተርናሽናል የሪያል ማድሪድ ተጫዋች  ከራሱ የሜዳ ክልል (ከ65 ሜትር  ርቀትላይ) ያስቆጠረው አስገራሚ ግብ  በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኗል።

ቱርካዊው ኢንተርናሽናል የሪያል ማድሪድ ተጫዋች አርዳ ጉለር
ቱርካዊው ኢንተርናሽናል የሪያል ማድሪድ ተጫዋች  ከራሱ የሜዳ ክልል (ከ65 ሜትር  ርቀትላይ) ያስቆጠረው አስገራሚ ግብ  በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኗል።ምስል፦ Jeenah Moon/REUTERS

ማድሪድ ኤልቼን 4 ለ 1 ባሸነፈበት ጫወታ ጉለር በ89ኛው ደቂቃ ነበር አስደናቂዋን ጎል በማስቆጠር የክለቡን የጎል ,መጠን  አራት ያደረሰው። በሊጉ በሁለቱ ፈረሶች መካከል የሚደረገው ትንቅንቅ ሲቀጥል ባርሴሎና ትናንት እሁድ በሜዳው ሴቪያን አስተናግዶ በሰፊ የጎል ልዩነት 5 ለ 2 ማሸነፍ ችሏል። በዚህም ከሪያል ማድሪድ ጋር የነበረውን የነጥብ ልዩነት ወደ አራት በማሳደግ ሊጉን በ70 ነጥቦች ይመራል።


ቡንደስ ሊጋ 


በጀርመን ቡንደስ ሊጋ ወደ ባይ አሬና የተጓዘው የሊጉ መሪ ባየር ሙኒክ ሁለት ተጫዋቾችን በቀይ ካርድ ቢያጣም ነጥብ ተጋርቶ ከመመለስ አላገደውም ። በሊጉ በስድስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ባየር ሊፈርኩሰን ኋላ ላይ በ9 ተጫዋቾች የቀረውን ሙኒክን መርታት ተስኖት ነጥብ ተጋርቶ ለመውጣት ሲገደድ ለሙኒኮች ግን ሙገሳ አስገኝቶላቸዋል። ሊጉን ባየር ሙኒክ በ9 ነጥብ ልዩነት በ67 ነጥቦች ይመራል። ዶርትሙንድ ይከተለዋል። 

ባየር ሊፈርኩሰን ከባየር ሙኒክ ያደረጉት ግጥሚያ
በጀርመን ቡንደስ ሊጋ ወደ ባይ አሬና የተጓዘው የሊጉ መሪ ባየር ሙኒክ ሁለት ተጫዋቾችን በቀይ ካርድ ቢያጣም ነጥብ ተጋርቶ ከመመለስ አላገደውም ። ምስል፦ Axel Kohring/BEAUTIFUL SPORTS/picture alliance


ቻምፒየንስ ሊግ 


በአውሮጳ ቻምፒየንስ ሊግ ሩብ ፍጻሜ ለመግባት የሚደረገው ትንቅንቅ ሲቀጥል ከነገ ማክሰኞ ጀምሮ ሁለተኛ ዙር ጫወታዎች ይስተናገዳሉ ። 
ነገ ማክሰኞ ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ ስፖርቲን ቦዶ ግሊምትን ሲኢስተናግድ በመጀመሪያው ዙር የደረሰበትን መራር የ3 ለ 0 ሽንፈት ለመቀልበስ ይታገላል። ምሽት አምስት ሰዓት ላይ  በተመሳሳይ ሰዓት ሶስት ጫወታዎች ሲደረጉ ማንችስተር ሲቲ ሪያል ማድሪድን የሚያስተናግድበት ጫወታ ትኩረት ስቧል። በመጀመሪያው ጫወታ የ 3 ለ 0 ሽንፈት የተከናነበው ሲቲ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ውጡቱን ይቀለብስ ይሆን ፤ ይጠበቃል።

አርሴናል በመጀመሪያ የሻምፒየንስ
አርሴናል በመጀመሪያው ጫወታ ከሜዳው ውጭ ነጥብ ተጋርቶ በመመለሱ የተሻለ ግምት ምስል፦ Ulrik Pedersen/NurPhoto/picture alliance

 

በተመሳሳይ ሰኦት አርሴናል ከባየር ሊቨርኩሰን እናዲሁም ቼልሲ ከፓሪሰን ዤርሜ ይጋጠማሉ ። አርሴናል በመጀመሪያው ጫወታ ከሜዳው ውጭ ነጥብ ተጋርቶ በመመለሱ የተሻለ ግምት ሲያገኝ ቼልሲ የደረሰበትን የ5 ለ 2 መራር ሽንፈት ለመቀልበስ በስታንፎርድ ብሪጅ ግንባር ይፋለማል። ግጥሚኢው የፊታችን ረቡዕ ቀጥሎ ሲደረግ ባርሴሎና ኒውካስል ዩናይትድን እንዲሁም ቶተንሃም አትሌቲኮ ማድሪድን የሚያስተናግዱበት ጫወታዎች  የሩብ ፍጻሜ ተፋላሚ ክለቦችን ይለያሉ ። 

ታምራት ዲንሳ

ጸሐይ ጫኔ