1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መኢአድ በሰሞኑ የመንግሥት እርምጃ ላይ

ዓርብ፣ ኅዳር 7 2011

መኢአድ ዛሬ በጽህፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ መንግሥት ሰሞኑን በሙስናና እና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ጠርጥሮ የያዛቸውን የቀድሞ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ለህግ ማቅረብ መጀመሩ ተጠናክሮ መቀጠል አለበትም ብሏል። ለመንግስት እርምጃ ተግባራዊነትም የአፍሪቃ ህብረት እና የተመድ እንዲሁም ጎረቤት ሀገራትም እገዛ እንዲያደርጉ ጠይቋል።

https://p.dw.com/p/38Ot8
Logo Äthiopien Opposition Partei AEUP

የመኢአድ መግለጫ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ መንግሥት መውሰድ የጀመረው የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ እርምጃ በጎ ጅምር ነው ሲል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ አወደሰ። መኢአድ ዛሬ በጽህፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ መንግሥት ሰሞኑን በሙስናና እና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ጠርጥሮ የያዛቸውን የቀድሞ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ለህግ ማቅረብ መጀመሩ ተጠናክሮ መቀጠል አለበትም ብሏል። ለመንግስት እርምጃ ተግባራዊነትም የአፍሪቃ ህብረት እና የተመድ እንዲሁም ጎረቤት ሀገራትም እገዛ እንዲያደርጉ ጠይቋል። በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ድርጅቱ በተለያዩ አካባቢዎች ስላካሄዳቸው እንቅስቃሴዎች እና ስለ ከፈታቸው አዳዲስ ቢሮዎችም ገለጻ አድርጓል። መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ወኪላችን ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።  


ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ