የመንግስት ኩባንዮችን የመሸጥ ዕቅድ
ሐሙስ፣ መስከረም 8 2012ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግስት የሚቆጣጠራቸዉን ትላልቅ ኩባንዮች በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ለመሸጥ ማቀዱ አሁንም ድጋፍና ተቃዉሞ እየተፈራረቀበት ነዉ።ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ በተደረገ ዉይይት ላይም የኩባንዮቹ መሸጥ የሐገሪቱን ምጣኔ ሐብት ለማሳደግና የግሉን ባለሐብት ተሳትፎ ለማበረታት ጠቃሚ ነዉ ባዮች ባንድ ባኩል፣ የለም ሽያጩ ከሥራ አጥነት፣ሉዓላዊነትን እስከማጋለጥ የሚደርስ ችግር ያስከትላል ባዮች በሌላ በኩል ጎራ ለይተዉ ተከራክረዋል።የማሕበራዊ ጥናት መድረክ የተሰኘዉ ተቋም ያዘጋጀዉን ዉይይት የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ተከታትሎታል።
ሰለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ