1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ

ቅዳሜ፣ ግንቦት 6 2014

መንግሥት ከሕወሓት የሚቃጣ የትኛውንም ዓይነት ጥቃት ለመመከት በየትኛውም ጊዜ ሙሉ ዝግጁነት፣ ዐቅም እና ብቃት አለው ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለፀ። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትር ለገሰ ቱሉ መንግሥታቸው ከውስጥም ከውጪም የሚቃጣ የትኛውንም ዓይነት ጥቃት ለመመከት ዝግጁ ነው ብለዋል።

https://p.dw.com/p/4BJHi
Äthiopien | Dr. Legesse Tulu - Kommunikationsminister
ምስል Seyoum Getu/DW

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ

መንግሥት ከሕወሓት የሚቃጣ የትኛውንም ዓይነት ጥቃት ለመመከት በየትኛውም ጊዜ ሙሉ ዝግጁነት፣ ዐቅም እና ብቃት አለው ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለፀ።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትር ለገሰ ቱሉ መንግሥታቸው ከውስጥም ከውጪም የሚቃጣ የትኛውንም ዓይነት ጥቃት ለመመከት ዝግጁ ነው ብለዋል።

ፖለቲካዊ ይዘት ባላቸው መገፋፋቶች ምክንያት እየጠፋ ያለን የሰው ሕይወትና የንብረት ውድመትን ለመግታት ብሎም አገራዊ አንድነትን ለማስከበር በሁሉም ክልሎች የተቀናጀ ያሉት እርምጃ እየተወሰደ መሆኑንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል ።

ሕወሓት አሁንም የአፋር እና የአማራ ክልል ወረዳዎችን በኃይል እንደያዘ መሆኑን የገለፁት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ መንግሥት ወደ ትግራይ የሚልከውን የሰብዓዊ እርዳታ እንደማያቋርጥ አስታውቀዋል። ይሁንና በመጪው ክረምት የትግራ ሕዝብ የመኸር አዝመራ ግብዐት ካላገኘ ይበልጥ ለረሃብ ሊጋለጥ ይችላል የሚል ሥጋት በመንግሥት በኩል እንዳለ ጠቅሰው ሕወሓት ጦርነትን ከመጎሰም እንዲቆጠብ አሳስበዋል።

 

ሰለሞን ሙጬ

ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር