የመንግሥት ኃይሎች በአማራ ክልል በርካታ ቦታዎችን መቆጣጠራቸው
ረቡዕ፣ ኅዳር 22 2014ማስታወቂያ
በሰሜን ኢትዮጵያ በቀጠለው ጦርነት የመንግሥት ኃይሎች የጦር ስልታዊ ጠቀሜታው ከፍ ያለ ነው የተባለለት የሰሜን ወሎ ጋሸና እና ሌሎች አከባቢዎችን መቆጣጠራቸው ተገለጸ። የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ የመንግሥት ኃይሎች ድል ቀንቷቸው ወደ ፊት እየገሰገሱ መሆኑን አረጋግጠዋል። ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ከሰሜን ወሎ ሁለት ግንባሮች በተጨማሪ በሰሜን ሸዋም የመከላከያ ሠራዊቱ እና ሌሎች የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ድል አስመዝግበው የተለያዩ አከባቢዎችን ከህወሃት ኃይሎች ማስለቀቅ መቻላቸውንም አመልክተዋል።
ስዩም ጌቱ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ