1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመን ላይ መላወሻ ያጡት ኢትዮጵያውያን ተሰዳጆች

ሰኞ፣ ሐምሌ 29 2011

ከምሥራቅ አፍሪቃ በርካታ ስደተኞች ወደ መካከለኛው ምሥራቅም ሆነ አውሮጳ ለመግባት ሲነሱ ባሕር ማቋረጥ ግድ ይሆንባቸዋል። የዶይቼ ቬለዋ ፋኒ ፋክሻር እንደምትለው በተለይ ያልታወቁ እና ርካሽ ዋጋ ለሕገወጥ ሰው አሸጋጋሪዎች ከፍለው ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሚጓጓዙባቸው መንገዶች በሜዲትራኒያን ባሕር ላይ ከሚያጋጥማቸው ችግር የባሰ አደገኞች ሆነዋል።

https://p.dw.com/p/3NNHB
Jemen Aden illegale Migranten aus Afrika
ምስል picture-alliance/Photoshot/M. Abdo

«ስደተኞች በጦርነት መካከል»

 አብዛኞቹ በኤደን ባሕረ ሰላጤ በኩል በአደገኛ መልኩ አቋርጠው የብስ ቢረግጡም እግራቸው የሚያርፈው በጦርነት እየተተራመሰች በምትገኘው የየመን ግዛት ላይ ነው። በቅርቡ እንዲህ ከሞት ጋር ተጋፍጠው በስቃይ ተጉዘው ወደ የመን የገቡ እና መድረሻ ያጡ ኢትዮጵያውያን የሚገኙበትን ሁኔታ መሠረት በማድረግ የአፍሪቃውያን ስደተኞችን ዕጣ ፈንታ የቃኘችበትን ዘገባ የበርሊኑ ወኪላችን እንደሚከተለው አጠናቅሮታል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ