1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመተከል ዞን የፀጥታ ችግር በምሁራን እይታ 

ሰኞ፣ ጥቅምት 2 2013

ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የሰላምና ደህንነት ጥናት፣የፈደራሊዝምና የህግ ባለሞያዎች እንዳሉት የችግሩ ዋነኛ ምክንያቶች  የአመራር ችግር፣ የፖለቲካ ጥቅም  ግጭቶች፣እንዲሁም  ችግሩን የመፍታት ፍላጎት አነስተኛ መሆን ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።በአካባቢው የሚኖሩ ህዝቦችን ጥያቄ መመለስ፣በዞኑ የፖለቲካ ፍላጎት ካላቸው አካላት ጋር መመካከርም ይበጃል ብለዋል

https://p.dw.com/p/3jozP
Karte Äthiopien Metekel EN

የመተከል ዞን የፀጥታ ችግር በምሁራን እይታ 

በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ተደጋግሞ የሚከሰተውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት በአካባቢው የሚኖሩ ህዝቦችን ጥያቄ መመለስ፣ በዞኑ የፖለቲካ ፍላጎት ካላቸው አካላት ጋር መመካከር ፣ ዘላቂ ሰላም ማስፈን የሚያስችሉ አማራጮች መሆናቸውን ምሁራን አስታወቁ። ዶቼቬለ በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው የሰላምና ደህንነት ጥናት፣ የፈደራሊዝም እና የህግ ባለሞያዎች በሰጡት አስተያየት የችግሩ ዋነኛ ምክንያቶች  የአመራር ችግር፣ የፖለቲካ ጥቅም  ግጭቶች ፣ እንዲሁም  ችግሩን የመፍታት ፍላጎት አነስተኛ መሆን ናቸው ሲሉ ተናግረዋል። 

 


ነጋሳ ደሳለኝ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ