1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመተከል ዞን የጸጥታ ሁኔታ

እሑድ፣ ሚያዝያ 9 2014

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ከ240 በላይ ታጣቂዎች እጅ መስጠታቸውን አካባቢውን ለማረጋጋት የተቋቋመው የጸጥታ እዝ አስታውቋል። የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ግራኝ ጉደታ የመተከልን ችግር በሰላማዊ መንገድ በመፍታት ሁሉንም ያሳተፈ እርቅ እንዲወርድ የተጀመረው ጥረት ዕክል እየገጠመው እንደሚገኝ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/4A1fZ
Karte Äthiopien Metekel EN

የመተከል ዞን የጸጥታ ሁኔታ

የመተከል ኮማንድ ፖስት በተለያዩ ጊዜያት የጉሙዝ ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ እጅ እየሰጡ እንደሚገኙ እየገለጸ ይገኛል፡፡ በትናንትናው ዕለት ከ240 በላይ ታጣቂዎች እጅ መስጠታቸውን አሳውቋል፡፡ በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የጉሙዝ ዴሞክረሲያዊ ንቅናቄ የፖለቲካ ድርጅት በበኩሉ ኮማንድ ፖስት በመተከል ዳንጉር፣ድባጢ እና ቡለን ወረዳ  ውስጥ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ሚያዚያ 2 እና 3 ጉዳት ማድረሱን ገልጸዋል፡፡ ድርጅቱ በኮማንድ ፖስት ላይ ያቀረበውን ቅሬታ አስመልክቶ ከአስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት አልቻለም፡፡ ነገር ግን በዞኑ በህገ ወጥ መንገድ ታጥቆ በሚንቀሳቀስና በሰላማዊ መንገድ እጅ በማይሰጥ ሀይል ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ኮማንድ ፖስቱ ከዚህ በፊት ለዲዳቢሊው ገልጸዋል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የጸጥታ ችግር ከሚስተዋልባቸው ስራፍዎች በመካከል ካማሺ ዞን ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የተደረጉ ጥረቶች የተሻለ ለውጥ ማስገኘቱ ተገልጸዋል፡፡ ለረጅም ጊዜያት የሰላም መናጋት ምክንያት በአስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር ስር በሚገኘው መተከል ዞንም ሰላም ለማስፈን መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብሎ በርካታ ታጣቂዎች እጅ እየሰጡ እንደሚገኙ የዞኑ አስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር አስታውቋል፡፡ በትናትናው ዕለትም ከ240 በላይ ታጣቂዎች በዞኑ ዳንጉር ወረዳ እጅ መስጠታቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ በማህበራዊ መገናኛ ዜው አመክልቷል፡፡

የጉሙዝ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ግራኝ ጉዴታ በዞኑ ያለው ችግር በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታና ሁሉንም ያሳተፈ ዕርቅ እንዲወርድ የጀመሩት ጥረት በተለያዩ ምክንያች እክል እንደገጠመው ገልጸዋል፡ በዞኑ ዳንጉር ወረዳን ጨምሮ በሶስት ወረዳዎች ውስጥ አስቸኳይ ጊዜ አስተዳደሩ በሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን እና ይህም  ለታሰበው እርቅ እንቅፋት እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም ግንባታ ጸጥታ ቢሮ ኃላፊና የአስቸኳይ ጊዜ አስተዳደሩ አባል አቶ አብዩት አልቦሮ ከዚህ ቀደም በሰጡን ማብራሪያ በዞኑ በሰላም መንገድ እጅ የማይሰጡና ወደ ዕርቅ መንገድ ማይመጡ ታጣቂዎች ላይ ህግ ማስከበር ስራ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ ከዚህ ቀደም  በመቶዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ የመንግስትን ጥሪ ተቀብሎ የተሀድሶ ስጠልና መውሰዳቸውን ጠቁመዋል፡፡ ሰላማዊ ጥሪን የማይቀበሉ የተወሰኑ  ግለሰቦች የሚፈጥሩትን ህገ ወጥ እንቅስቃሴን ተከታትሎ ኮማንድ ፖስቱ ህግ ያስከብራል ብሏል፡፡

የዞኑ አስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር የጉህዴን ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ እጅ እየሰጡ እንደሚገኙና እስካሁን ከ500 በላይ ታጣቂዎች እጅ መስጠታቸው ገልጸዋል፡፡ ጉህዴን በበኩሉ ታጣቂዎቹ በራሳቸው መንገድ የተደራጁና ከፓርቲው ጋር የሚገናኝ ታጣቂ አለመኖሩን ከዚህ ቀደም መግለጹን ዘግበን ነበር፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

እሸቴ በቀለ