1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመቀሌ የኃይል ለዉጥና ቀድሞዉ ወታደር አስተያየት

ማክሰኞ፣ ሰኔ 22 2013

ቀድሞዉ የኢትዮጵያ ሠራዊት ማሕበር ፕሬዝደንት የሐምሳ ዓለቃ ብርሐኑ አማረ እንደሚሉት የኢትዮጵያ ሠራዊት መቀሌን ለቅቆ የወጣበት  በርካታ ወታደራዊ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ።

https://p.dw.com/p/3vm1R
Tigray-Konflikt | Militär in Addis Abeba
ምስል Minasse W. Hailu/AA/picture alliance

የኢትዮጵያ ጦር ከመቀሌ የወጣበት ቢሆናዊ ምክንያት

የኢትዮጵያ ጦር የትግራይ ክልል ርዕሠ-ከተማ መቀሌን ለቅቆ የወጣዉ ከሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት) ታጣቂዎች ጋር ዉጊያ ገጥሞና ተሸንፎ ሳይሆን «ታክቲካዊ ማፈግፈግ» ሊሆን እንደሚችል አንድ የቀድሞ የኢትዮጵያ ሠራዊት ባልደረባ አስታወቁ።የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ሠራዊት ማሕበር ፕሬዝደንት የሐምሳ ዓለቃ ብርሐኑ አማረ እንደሚሉት የኢትዮጵያ ሠራዊት መቀሌን ለቅቆ የወጣበት  በርካታ ወታደራዊ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ።ሐምሳ ዓለቃ ብርሐኑ ከጠቀሷቸዉ ከምክንያቶች ጥቂቶቹ ጦሩ እንደገና ለመደራጀት፣መንግሥት እንዳለዉ የተናጥል ተኩስ አቁም በመታወጁና የግብርና ወቅትን ከግምት በማስገባት፣ የትግራይ ሕዝብና ሕወሓት ያላቸዉን ቁርኝት በመገንዘብ ወይም ዓለም አቀፍ ጫናዎች በመጠናከራቸዉ የሚሉ ይገኙባቸዋል። 

ነጋሽ መሐመድ

ታምራት ዲንሳ