1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመቀሌ ነዋሪዎች አስተያየት

ሐሙስ፣ ሰኔ 20 2011

ባሳለፍነው የሳምንት መጨረሻ ቅዳሜ ዕለት በጠባቂያቸው መገደላቸው የተነገረው የጀነራል ሰዓረ መኮንን እና በጡረታ ላይ የነበሩት ሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ የቀብር  ትናንት መቀሌ ከተማ ላይ  ሥርዓተ ቀብራቸው  ሲከናወን በርካታ ክስተቶች መታየታቸው ተነገረ።

https://p.dw.com/p/3LCYw
Äthiopien Trauerfeier für General Seare Mekonnen
ምስል picture-alliance/AP Photo/M. Ayene

በቀብር ሥርዓቱ ላይ የተገኙ ወገኖች አስተያየት

 በወቅቱ ለቀብር የወጡት እጅግ በርካታ ወጣቶች የተለያዩ መፈክሮች ሲያሰሙ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ለቀብር  በስፍራው የተገኙት የትግራይ ዴሞክራሲያ ትብብር ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄም ችግር አጋጥሟቸው እንደነበር ተሰምቷል። በትግራይ የፀጥታ ኃይሎች ታስረዋል የተባለላቸው ከህወሀት  አንጋፋ መስራቾች አንዱ የነበሩት ዶክተር አረጋዊ ዛሬ አለመታሰራቸውን ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን የገለፁ ሲሆን፤ በጉዳዩ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ለመረዳት ችለናል። የትናንቱን የመቀሌ ክስተት ያካተተው የዘጋቢያችን  ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ ዝርዝር ዘገባ እነሆ።

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ