1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የሕዳሴ ግድብ ዉኃ ሙሌት

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 28 2012

ኢትዮጵያ ግብዱቡን የምትሞላበትን ጊዜ እንድታራዝም ግብፅና ሁለቱን ወገኖች እናደራድራለን የሚሉት የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት በቀጥታም በተዘዋዋሪም ግፊት እያደረጉ መሆናቸዉ በሰፊዉ እየተነገረ ነዉ

https://p.dw.com/p/3brch
Sudan - Roseires Damm
ምስል Getty Images/AFP/E. Hamid

የሕዳሴ ግድብ ሊሞላ ነዉ


ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ በምታስገነባዉ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ሰበብ ከግብፅ ጋር የገጠመችዉ ዉዝግብ እልባት ባያገኝም ግድቡን በመጪዉ ክረምት መሙላት እንደምትጀምር የዉሐ ሚንስቴር አስታወቁ።ኢትዮጵያ ግብዱቡን የምትሞላበትን ጊዜ እንድታራዝም ግብፅና ሁለቱን ወገኖች እናደራድራለን የሚሉት የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት በቀጥታም በተዘዋዋሪም ግፊት እያደረጉ መሆናቸዉ በሰፊዉ እየተነገረ ነዉ።የኢትዮጵያ የዉኃ፣መስኖና ኃይል ማመንጪያ ሚንስትር ስለሺ በቀለ እንዳሉት ግን ግድቡ ከመጪዉ ኃምሌ ጀምሮ ዉኃ ይሞላል።አንድ ባለሙያ እንዳሉት ደግሞ ዘንድሮ የሚሞላዉ ወኃ ሁለት ተርባይኖች ማንቀሳቀስ ይችላል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ