1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሕይወት ዘመን የራድዮ ባለውለታዎች

እሑድ፣ የካቲት 13 2014

አንጋፋ ጋዜጠኞች ሃሊማ ኡስማን፣ አለምነህ ዋሴ እና ነጋሽ መሃመድ እንግዶቻችን ናችው። ውድ የመዝናኛ ዝግጅት ታዳሚዎች። ሦስቱም ሰሞኑን በተከበረው ዓለም አቀፍ የራድዮ ቀን የሕይወት ዘመን የራድዮ ባለውለታ ተላሚዎች።

https://p.dw.com/p/47FQM
Deutschland äthiopischer Friedensminister Muferihat Kamil Ahmed im Interview mit Negash Mohammed
ምስል DW

መዝናኛ፦ ተሸላሚዎቹ ጋዜጠኞች

አንጋፋ ጋዜጠኞች ሃሊማ ኡስማን፣ አለምነህ ዋሴ እና ነጋሽ መሃመድ እንግዶቻችን ናችው። ውድ የመዝናኛ ዝግጅት ታዳሚዎች። ሦስቱም ሰሞኑን በተከበረው ዓለም አቀፍ የራድዮ ቀን የሕይወት ዘመን የራድዮ ባለውለታ ተላሚዎች። በተለይ ነጋሽ እና አለምነህዋሴ እርስ በእርሳቸው እየተጠያየቁ ትውስታቸውን ያጋሩናል። 

በቄለም ወለጋ ደምቢደሎ ተወልዳ ያደገችው ሃሊማ ኡስማን የተማረችው የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ቢሆንም አዲስ አበባ ላይ በተመረቀችበት ሥራ ማግኘት አልቻለችም።  በወቅቱ በለገዳዲ የትምህርት በራድዮ በመረጃ ለቀማ ሥራ ተቀጠረች። በጣቢያው አንዳንድ ጽሑፎች በማንበብ የጋዜጠኝነት ትውውቅ ከጀመረች በኋላ በኢትዮጵያ ራድዮ የኦሮምኛ ዝግጅት ክፍል ተቀጥራ ዜና እና ፕሮግራሞችን በማቅረብ ተወዳጅነትን አትርፋለች። በተለይ በመዝናኛ ዝግጅት ይቀረቡ በነበሩ የራድዮ ድራማዎቸ ተወዳጀነትን አእንዳተረፉላት ትናገራለች። ሰሞኑን በተከበረው ዓለም አቀፍ የራድዮ ቀን የሕይወት ዘመን የራድዮ ባለውለታ ተሸላሚ መሆኗ እንዳስደሰታት ገልጻልናለች።

የኢትዮጵያ ራድዮ ለኔ ባለውለታዬ ነው የምትለው ሃሊማ ኦስማን በሙያው ብቁ እንድትሆን ባልደርቦቿ ከፍተኛ አስተዋጻኦ እንዳደረጉላት እና በኋላም ጣቢያው ጋዜጠኝነት እንዳስተማራት በምስጋና ታወሳዋለች። አሁን የተሰጣት ሽልማትም እሷንና ወጣት ጋዜጠኞችን እንደሚያነቃቃ በማከል።

አንጋፎቹ የቀድሞ ባልደርቦች፣ የራድዮ ባለውለታዎችና የሕይወት ዘመን የራድዮ አገልግሎት ተሸላሚዎች ነጋሽ መሃመድና አለምነህ ዋሴ መድረኩን ራሳቸው ወስደው ትውስታቸውን እርስ በርስ እንዲህ አወጉን። 


የዘንድሮዎቹን የሕይወት ዘመን የራድዮ ባለውለታ ተሸላሚዎች ነጋሽ መሃመድ፣ ሃሊማ ኦስማንና አለምነህ ዋሴን መልካም የስራ ዘመን እንመኛለን።

DW-Interview mit Frank-Walter Steinmeier
ጋዜጠኛ ነጋሽ መሐመድ ከጀርመን ፕሬዝደንት ቫልተር ሽታይን ማየርምስል DW/R. Oberhammer
Äthiopien Radio Day Award von DW Negash Mohammed, Alemneh Wase
ጋዜጠኛ ዓለምነህ ዋሴምስል Radio Day Award
Äthiopien Radio Day Award Halima Osman
ጋዜጠኛ ሃሊማ ኡስማን ምስል Radio Day Award

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 

ሽዋዬ ለገሠ