1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሕዝብ አስተያየት በመንግስት ተደራዳሪዎች ላይ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 21 2014

በምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር የሚመራዉ ኮሚቴ የመረጃ፣የፍትሕ፣ የወታደራዊና ዲፕሎማሲ ባለስልጣናትና ባለሙያዎችን ያካተተ ነዉ።ሕወሓትን የሚወክሉትን ተደራዳሪዎች ማንነት እስካሁን አላሳወቀም።

https://p.dw.com/p/4DNTf
Äthiopien Addis Abeba Stadtansicht
ምስል Seyoum Getu/DW

የድርድር ሐሳብ፣ ኮሚቴና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አስተያየት

 

የኢትዮጵያ የፌደራል መንግስት ከሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ጋር ባቀደዉ ድርድር የሚካፈሉ 7 አባላት ያሉት ኮሚቴ መሰየሙን አስታዉቋል።በምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር የሚመራዉ ኮሚቴ የመረጃ፣የፍትሕ፣ የወታደራዊና ዲፕሎማሲ ባለስልጣናትና ባለሙያዎችን ያካተተ ነዉ።ሕወሓትን የሚወክሉትን ተደራዳሪዎች ማንነት እስካሁን አላሳወቀም።የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላማዊ ድርድር መዘጋጀቱንና የሰየመዉ ኮሚቴ ስብዝር በተመለከተ አዲስ አበባና አዉሮጳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንን አነጋግረናል።በመጀመሪያ የአዲስ አበባዉ ዘጋቢያችን ያነጋገራቸዉ ነዋሪዎች ያሉትን እናሰማችሁ።በተለያዩ የአዉሮጳ ሐገራት የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችም ሁለት ዓመት ግድም ያስቆጠረዉ ጦርነት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ተፋላሚ ኃይላት ፍላጎት ማሳየታቸዉን ደግፈዉታል።ይሁንና ካነጋገርናቸዉ የትግራይ ተወላጆች አንዳዶቹ ሰላማዊዉ ድርድር እንዲሳካ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ የጣለዉን እገዳ ማንሳት አለበት ሲሉ፣ ሌሎች ደግሞ የፌደራሉ መንግስት ለሰላም መቆሙን ይጠራጠራሉ።

ሰለሞን ሙጬ

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ