የሕዝብ ቆጠራና የአማራ ፓርቲ ተቃዉሞ
ረቡዕ፣ የካቲት 13 2011ማስታወቂያ
በመጪዉ መጋቢት ማብቂያ ኢትዮጵያ ዉስጥ ሊደረግ የታቀደዉ የሕዝብና የቤቶች ቆጠራ እንዲራዘም በአማራ መስተዳድር የሚንቀሳቀሰዉ ተቃዋሚ ፓርቲ ጠየቀ። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እንደሚለው ከአስራ ሰወስት ዓመት በፊት ግድም የተደረገው የሕዝብ ቆጠራ ውጤት የተሳሳተ በመሆኑ መሠረዝ አለበት። ያለፈው እስኪስተካከል ለመጋቢት የተጠራዉ ቆጠራም መደረግ የለበትም። ፓርቲዉ የ1999ኙን የሕዝብ ቆጠራ ውጤትን «አስነዋሪ» ብሎታልም።
ዓለምነው መኮንን
ነጋሽ መሀመድ
ሸዋዬ ለገሰ