1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሕወሓትና የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አንድነትና ልዩነት

ማክሰኞ፣ ኅዳር 9 2012

አረና ትግራይ ለፍትሕና ለሉዓላዊነት ፓርቲ የኢሕአዴግን መዋሐድ ደግፎ፣ ሕወሓትም ዉሕደቱን መቀበል ነበረበት ብሏል።በቅርቡ ከተመሰረቱት ሁለት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሳልሳዊ ወያኔ የተባለዉ የሕወሓትን አቋም ሲደግፍ፣ የታላቅዋ ትግራይ ብሔራዊ ሸንጎ ወይም ባይቶና ፓርቲ ግን በኢሕአዴግ ዉሕደት ላይ የተፈጠረዉን ልዩነት «አደገኛ» ብሎታል

https://p.dw.com/p/3TJMY
Emblem der Tigray People's Libration Font (TPLF)

የሕወሓትና የተቃዋሚዎቹ አንድነትና ልዩነት

የትግራይ ገዢ ፓርቲ ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የኢሕአዴግን ዉሕደት መቃወሙ በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን እሶስት  ገምሶ እያነጋገረ ነዉ።በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ 3 ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ አረና ትግራይ ለፍትሕና ለሉዓላዊነት ፓርቲ የኢሕአዴግን መዋሐድ ደግፎ፣ ሕወሓትም ዉሕደቱን መቀበል ነበረበት ብሏል።በቅርቡ ከተመሰረቱት ሁለት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሳልሳዊ ወያኔ የተባለዉ የሕወሓትን አቋም ሲደግፍ፣ የታላቅዋ ትግራይ ብሔራዊ ሸንጎ ወይም ባይቶና ፓርቲ ግን በኢሕአዴግ ዉሕደት ላይ የተፈጠረዉን ልዩነት «አደገኛ» ብሎታል።የመቀሌዉ ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለስላሴ እንደዘገበዉ ስለ ዉሕደቱ የሕወሓት ሥራ-አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትንና የፅሕፈት ቤት ኃላፊዎችን ለማነጋገር በስልክም በአካልም ቢሞክር አልተሳካለትም።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ