1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰሚያጣዉ ስሞታ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 24 2010

የጠቅላይ ጉባኤዉ ኃላፊዎች እንደሚሉት አሁንም ፀሎታቸዉን ጨርሰዉ ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱ ሑጃጆችን የመልስ ጉዞም አየር መንገዱ እያስተጓጎለ ነዉ።የአየር መንገዱ ባለሥልጣናት ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸዉ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

https://p.dw.com/p/343ct
Saudi-Arabien Hadsch in Mekka
ምስል Reuters/Z. Bensemra

(Beri.Jeddah) Eth.Hajji pligrames-EAL - MP3-Stereo

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለኢትዮጵያዉያን ሑጃጆችን አሁንም እያንገላታ መሆኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ጉባኤ ባለሥልጣናት አስታወቁ።የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኢትዮጵያዉያን ሑጃጆችን ከተገቢዉ ዋጋ አስከፍሎም፤ከአዲስ አበባ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ማጓዝ በሚገባዉ ዕለት ባለማጓዙ፤ ምግብ እና ማደሪያ ባለማቅረቡ ምክንያት ከፍተኛ ወቀሳ እና ትችት ሲሰነዘርበት ነበር።የጠቅላይ ጉባኤዉ ኃላፊዎች እንደሚሉት አሁንም ፀሎታቸዉን ጨርሰዉ ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱ ሑጃጆችን የመልስ ጉዞም አየር መንገዱ እያስተጓጎለ ነዉ።የአየር መንገዱ ባለሥልጣናት ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸዉ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ጉባኤ ለጠቅላይ ሚንስቴር ፅሕፈት ቤት አቤት ማለቱን አስታዉቋል።የጂዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ነቢዩ ሲራክ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ