1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች በደቡብ ክልል 

ማክሰኞ፣ ግንቦት 6 2011

የደቡብ ክልል ከሦስት ሺህ በላይ የመንግሥት ሠራተኞች በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ተቀጥረው ሲያገለገሉ እንደተደረሰባቸው የክልሉ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት ዐስታወቀ።

https://p.dw.com/p/3IUH4
Äthiopien Mekonnen Desta, SNNPR
ምስል DW/S. Wegayehu

ከ3 ሺህ በላይ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች በደቡብ ክልል

ጽሕፈት ቤቱ እንዳስታወቀው ሠራተኞቹ በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች መቀጠራቸው ሊደርስባቸው የቻለው በክልል፣ በዞኖች እና በወረዳዎች በሚገኙ የአስተዳደር መዋቀሮች ውስጥ በተካሄደ የማጣራት ሥራ ነው። በሐሰተኝነት ከተለዩት ማስረጃዎች መካከል ከዲፐሎማ እስከ መጀመሪያ ዲግሪ  የሚደርሱ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች እንደሚገኙባቸው አንድ ከፍተኛ የጽ/ቤቱ የሥራ ኃላፊ ለዶይቸ  ቬሊ (DW)  ገልጠዋል።  

በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ሲገለገሉ ከነበሩት በክልል እና በወረዳ የአስተዳደር መዋቅሮች በከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት ላይ የተቀመጡ አመራሮችም እንሚገኙበት መግለጻቸውን ከሐዋሳ ሸዋንግዛው ወጋየሁ የላከልን ዘገባ ያስረዳል። እንዲህ ያለው ድርጊት እየተበራከተ መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን ከወንጀልነቱ አልፎ የትምህርት ጥራትን በመቀነስ፣ የተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ እንደሚያዛባ ምሁራን መግለጻቸውን ዘገባው አክሎ ጠቅሷል። 

ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ