የዙሪኩ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል
ሰኞ፣ ሐምሌ 29 2011ማስታወቂያ
ዙሪክ ስዊትዘርላንድ ውስጥ ባለፈው ሳምንት የተካሄደው 17 ተኛው «በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል»ባለፈው ቅዳሜ ተፈጽሟል።በእግር ኳሱ ውድድር «ኢትዮ ቡና ፍራንስ» ተጋጣሚውን የኢትዮ ሆላንድ ቡድን አሸንፎ የዘንድሮው ሻምፕዮና ሆኗል።በታዳጊ ወጣቶች ዘርፍ በተካሄደው ውድድርም ኢትዮ ፍራንስ አዘጋጁን የኢትዮ ዙሪክ ቡድን አሸንፎ ዋንጫውን ወስዷል። የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች በእንግድነት የተገኙበት የዘንድሮው ውድድር ከአምናው ጋር ሲነጻጸር የተሻለ እንደነበር አዘጋጆቹ ተናግረዋል።በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኘችው የፓሪስዋ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህ እንደታዘበችው በፌስቲቫሉ ሴቶችን የሚያሳትፉ ውድድሮች አልነበሩም። ዝርዝሩን ሳምንታዊው የስፖርት መሰናዶ ተጠናቅሮአል።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ኂሩት መለሰ