1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የልዩ ፖሊስ ጥቃት በመዩ ሙሉቄ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 8 2010

በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሀረርጌ በመዩ ሙሉቄ ወረዳ በሮጌ ቀበሌ በሳምንቱ መጨረሻ በሶማሊ ክልል ልዩ ፖሊስ አባላት ተገደሉ የተባሉ የ41 ሰዎች ስርዓተ ቀብር ትናንት ተፈጸመ።

https://p.dw.com/p/339jv
Äthiopien Stadt Jijiga
ምስል DW/T. Waldyes

የመዩ ሙሉቄ ወረዳ ኃላፊ አቶ አመዲን እስማኤል ለዶይቸ ቬለ እንደተናገሩት፣ በጥቃቱ ከተገደሉት መካከል ሽማግሌዎች ፣ አካል ጉዳተኞች እና የሁለት ወር ሕፃን ሳይቀር ይገኙባቸዋል። ብዙዎች የቆሰሉበትን፣ ንብረት የተዘረፈበትን እና መኖሪያ ቤቶች የተቃጠሉበትን ጥቃት በመሸሽ የተፈናቀሉት ደግሞ አሁን ወደ ወሲ ከተማ እየሄዱ መሆኑም ተረጋግጧል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ