1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሉሲ ቅጂ ለዩኔስኮ የመሰጠቱ ፋይዳ

ሐሙስ፣ ሰኔ 24 2013

ኢትዮጵያ በሚዳሰሱም ሆነ በማይዳሰሱ የዓለም ቅርሶች ያስመዘገበችው በርካታ ቅርሶች ቢኖራትም፤ በድርጅቱ ጽ/ቤት ውስጥ ግን የሚዳሰስ አንዳችም ወካይ ቅርስ አልነበራትም። ድንቅነሽን ልዩ ሴት ሲሉ የገለጿት የዩኔስኮ ዋና ኃላፊ ኦውድሬ አዞላይ ድርጅታቸው ይህን ቅርስ ለመያዝ በመቻሉ መደሰታቸውን እና ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስትም ምስጋና አቅርበዋል።

https://p.dw.com/p/3vtqB
Lucys Fossil Australopithecus afarensis
ምስል AP/picture alliance

የሉሲ ቅጂ ለዩኔስኮ የመሰጠቱ ፋይዳ

እድሜ ጠገቧ ቅሪተ አካል ድንቅነሽ ወይም ሉሲ ቅጂ ባለፈው ሳምንት አርብ ለተባበሩት መንግሥታት የትምሕርት፤ የሳይንስና የባህል ድርጅት በምህጻሩ(UNESCO)ተሰጥቷል። የቅሪተ አካሏ ቅጂ ርክክብ  ፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ በሚገኘው የዩኔስኮ ዋና መቀመጫ መሥሪያ ቤት በተካኼደ ልዩ ሥነ ሥርዓት ተፈጽሟል። በፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ፖርቹጋል፣ ሆሊ ሲ እና ሞናኮ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር እንዲሁም የዩኔስኮ የኢትዮጵያ ቋሚ መልእክተኛ አምባሳደር ኄኖክ ተፈራ ሻውል የድንቅነሽን ቅሪተ አካል ቅጂ ለዩኔስኮ ዋና ኃላፊ ኦውድሬ አዞላይ አስረክበዋል። አምባሰደር ኄኖክ ስለርክክቡ በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ «የእኛ የሰው ልጆች የጋራ ተምሳሌት የኾነችው ሉሲ ወይንም ድንቅነሽ ቅሪተ አካል ቅጂን በማስረከቤ እጅግ ደስታ ይሰማኛል» ብለዋል።
ዩኔስኮን ከመሰረቱ አገራት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ በሚዳሰሱም ሆነ በማይዳሰሱ የዓለም ቅርሶች ያስመዘገበችው በርካታ ቅርሶች ቢኖራትም፤ በድርጅቱ ጽ/ቤት ውስጥ ግን የሚዳሰስ አንዳችም ወካይ ቅርስ አልነበራትም። ድንቅነሽን ልዩ ሴት ሲሉ የገለጿት የዩኔስኮ ዋና ኃላፊ ኦውድሬ አዞላይ ድርጅታቸው ይህን ቅርስ ለመያዝ በመቻሉ መደሰታቸውን እና ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስትም ምስጋና አቅርበዋል። በሥነስርዓቱ ላይ  እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ1974 በአፋር ክልል ሐዳር በተሰኘ አካባቢ የድንቅነሽን (ሉሲ) ቅሪተ አካል በቊፋሮ ካገኙት የቅሪተ አካል ተመራማሪዎች መካከል አንዱ  ፈረንሳዊው ኢቪ ኮፓን ጨምሮ የመስኩ ተመራማሪዎች ሉሲ በሳይንሱ ዓለም ስላላት ጉልኅ ሚና ማብራሪያ ሰጥተዋል። የፓሪሷ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህ የርክክቡን ስነርዓትና የሉሲ ቅጂ ለዩኔስኮ መበርከቱ የሚኖረውን ፋይዳ በዛሬው የባህል መድረክ ዝግጅታችን ታስቃኘናለች።
ሐይማኖት ጥሩነህ 
ኂሩት መለሰ 
ነጋሽ መሐመድ