1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የለዛ ሽልማት ለኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ተሰጠ

እሑድ፣ ጥቅምት 9 2012

በየዓመቱ በተለይም በፊልምና ሙዚቃ ዘርፍ ሽልማት ከሚሰጡት መካከል አንዱ የሆነውና 9ኛው የለዛ ሽልማት ከ10 በላይ በሆኑ ዘርፎች ሽልማቱን በሳምንቱ አጋማሽ ሰጥቷል። በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ በቅርቡ ሕይወቱ ያለፈው ሙዚቀኛው ኤልያስ መልካ በእጅጉ ታስቦበታል።

https://p.dw.com/p/3RbBu
Äthiopien Leza Award in Addis Abeba
ምስል DW/S. Muchie

የለዛ ሽልማት ለኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ተሰጠ

የኢትዮጵያን የኪነ ጥበብ ሥራ እና ባለሙያዎችን የሚያበረታቱ፣ ተሽለው የተገኙትንም ለእውቅናባ ሽልማትሽ የሚያበቁ በጣት የሚቆጠሩ ዝግጅቶች ቢኖሩም ውጤታቸው ግን በየዓመቱ የተሻለ ሥራ ይዘው የሚቀርቡ ኪነጥበበኞችን እያፈሩ ይገኛሉ። በየዓመቱ በተለይም በፊልምና ሙዚቃ ዘርፍ ሽልማት ከሚሰጡት መካከል አንዱ የሆነውና 9ኛው የለዛ ሽልማት ከ10 በላይ በሆኑ ዘርፎች ሽልማቱን በሳምንቱ አጋማሽ ሰጥቷል። በሽልማቱ የዓመቱ ምርጥ ሙዚቃ፣ ምርጥ ነጠላ ሙዚቃ፣ የሙዚቃ ክሊፕ፣ የሙዚቃ አልበም፣ ምርጥ ተዋናይ እና ተዋናይት፣ ምርጥ የቴሌቪዥን ተከታታይ ፊልም፣ የዓመቱ ምርጥ ፊልም፣ የዕድሜ ልክ ተሸላሚ እና ሌሎች መስፈርቶች ላይ በዳኞች፣ በአድማጮችና በሁለቱ ጣምራ ድምጽ አሸናፊ የሆኑት ሽልማታቸውን ተረክበዋል። በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ በቅርቡ ሕይወቱ ያለፈው ሙዚቀኛው ኤልያስ መልካ በእጅጉ ታስቦበታል።

ሰለሞን ሙጬ

እሸቴ በቀለ