1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የለንደኑ የአፄ ኃይለሥላሴ ሐዉልት መፍረስ

ረቡዕ፣ ሰኔ 24 2012

በብሪታንያ ለንደን ከኢትዮጵያ ኤንባሲ የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ ያወረዱና ኃይል የቀላቀለ ተግባር የፈፀሙ በፖሊስ እየተፈለጉ ነዉ። በለንደን ከተማ ፓርክ የቆመን የአፄ ኃይለሥላሴን ሐዉልትን በማፈራረሳቸዉም እስከ 10 ዓመት ፅኑ እስራት ጠብቃቸዋል ተብሎአል።

https://p.dw.com/p/3eejw
London I Haile Selassie I Statue
ምስል Privat

የብሪታንያ ፖሊስ ወንጀለኞችን እየፈለገ ነዉ ተብሎአል

በብሪታንያ ለንደን በኃይል የተደራጁ ቁጥራቸዉ ከ 20 ያለነሰ ወጣቶች ትናንት በኢትዮጵያ ኤንባሲ ቅፅር ጊቢ ዉስጥ በመግባት በቅፅር ግቢ ዉስጥ በመግባት የተሰቀለ የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ በማዉረድ የፈፀሙት ኃይል የቀላቀለ ተግባር ብሎም በከተማዋ ፓርክ የሚገኝን የአፄ ኃይለሥላሴ ኃዉልትን ያፈረሱ ሰዎችን ተግባር የብሪታንያ ፖሊስ በቸልተኝነት እንደማያየዉ መግለጫ ገለፀ። በለንደን የኢትዮጵያ ኤንባሲ ምክትል የሚሲዮን መሪ አምባሳደር አባቢ ደምሴ ለዶቼ ቬለ እንደገለፁት ወጣቶቹ ኤንባሲ ገብተዉ ሰንደቃላማን ከተሰቀለበት ከማዉረድ በከተማዋ ያለን ሃዉልት ከማፍረስ በተጨማሪ ምሽት የኤንባሲ ሰራተኞች ሲወጡ ያልታወቀ ፈሳሺችን ቀላቅለዉ በኤንባሲ ሰራተኞች ላይ ለማፍሰስ ጥረት አድርገዉ በጠባቂ ዘቦች ድርጊቱ እምብዛም ሳይሳካ መቅረቱን ተናግረዋል። ፖሊስ ከቅርብ ሰዓታት በፊት በፎቶ በማስደገፍ ሦስት ሰዎችን እየፈለገ ነዉ ። ድርጊቱ እስከ አስር ዓመት ፅኑ እስራት ያስቀጣልም ተብሎአል። አዜብ ታደሰ በለንደን ከአምባሳደር አባቢ ደምሴ ጋር ተከታዩን ቃለ ምልልስ አድርጋለች።     

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ