1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

                   የለቅሶዉ መዘዝ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 18 2012

ኢትዮጵያ ዉስጥ በኮቪድ 19 የሞቱት የ4ኛው ሰው ቤተሰቦችን ለማስተዛዘን ለቅሶ ተቀምጠው የነበሩ ከ30 በላይ የመንደሩ ነዋሪዎች በኮሮና በተኅዋሲ መያዛቸዉን እርምጃዉን ከሚያስተባብሩ ወጣቶች አንዱ ገልጿል።መንደር 3 አንድ መቶ ያህል መኖሪያ ቤቶች ይገኛሉ ተብሎ ተገምቷል።

https://p.dw.com/p/3cnUZ
Äthiopien Addis Abeba Coronavirus Lockdown
ምስል DW/S. Muche

                   የለቅሶዉ መዘዝ

አዲስ አበባ ዉስጥ በልደታ ክፍለ ከተማ፣ በወረዳ 3 ፣ ቀጠና 5 ፣ መንደር 3 (በተለምዶ አብነት የሚባለው አካባቢ) የኮሮና ተሕዋሲ በርካታ ሰዎችን በመያዙ ምክንያት የአካባቢዉ ነዋሪዎች በሙሉ ከሌሎች አካባቢዎች ነዋሪዎች ጋር እንዳይገናኙ ታገዱ። እርምጃዉ የተወሰደዉ በነዋሪዎቹ ፈቃድና ይሁንታ ነዉ ተብሏል።የመንደሩ ነዋሪዎች ከወትሮ እንቅስቃሴቸዉ እንዲታቀቡ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲጠቀሙ ፖሊስ ጠንካራ ቁጥጥር እያደረገ ነዉ። በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችም ይህንን ስራ እያስተባበሩ መሆኑን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ ተመልክቷል።ኢትዮጵያ ዉስጥ በኮቪድ 19 የሞቱት የ4ኛው ሰው ቤተሰቦችን ለማስተዛዘን ለቅሶ ተቀምጠው የነበሩ ከ30 በላይ የመንደሩ ነዋሪዎች በኮሮና በተኅዋሲ መያዛቸዉን እርምጃዉን ከሚያስተባብሩ ወጣቶች አንዱ ገልጿል።መንደር 3 አንድ መቶ ያህል መኖሪያ ቤቶች ይገኛሉ ተብሎ ተገምቷል።
ሰለሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ