የሆሎኮስት 70ኛ ዓመት መታሰቢያ
ማክሰኞ፣ ጥር 19 2007ማስታወቂያ
የሶቪየት ሶሻሊስት ሪፐብሊክ ሕብረት ቀዩ ጦር የዛሬ ሰባ ዓመት በዛሬዉ ዕለት የአዉሽቪትዝ-ፖላንድን ማጎሪያ ጣቢያ ከናዚ እጅ ከማስለቀቁ በፊት በዚያ በትልቁ እስር ቤት ከአንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺህ ሰዎች በላይ በጋዝ ታፍነዉ ተገድለዋል። የጀርመኑ ርዕሰ ብሔር ዮአኺም ጋዉክ ዕለቱን ለማሰብ ለተሰበሰበዉ የጀርመን ምክር ቤት (ቡንደስታኽ) ባደረጉት ንግግር ዘረኛነት፤ ጥላቻና እሱን ተከትሎ የመጣዉ የዘር ማጥፋት የፋሽስቶች ዘመቻ መረሳት የለበትም በማለት ትዉልዱ እንዲያስብበት አስጠንቅቀዋል። የበርሊኑ ዘጋቢችን ይልማ ኃይለሚካኤል ዝርዝር ዘገባ ይኮልናል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ