1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የህወሓት ሌላ የሮኬት ጥቃት በባህርዳር   

ዓርብ፣ ኅዳር 11 2013

ህወሓት ትናንት ሌሊትባሕር ዳር ላይ የፈነዳው ሮኬትን የተኮስኩት እኔ ነኝ አለ። ፍንዳታዉ የተሰማዉ ሐሙስ ለሊት ለአርብ አጥብያ ከለሊቱ 7ሰዓት ከ40 ደቂቃ አካባቢ እንደሆነ ቦታዉ ላይ የነበሩ ሰዎች ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3lcYY
ምስል Alemenew Mekonnen/DW

የሮኬት ጥቃቱ ባህር ዳር ከተማ ላይ ያደረሰው ጉዳት የለም

ባህር ዳር ከተማ ከህወሓት የተተኮሰ ሮኬት ፍንዳታ ትናንት መሰማቱ ተነገረ። ፍንዳታዉ የተሰማዉ ሃሙስ ለሊት ለአርብ አጥብያ ከለሊቱ 7ሰዓት ከ40 ደቂቃ አካባቢ እንደሆነ ቦታዉ ላይ የነበሩ ሰዎች ተናግረዋል። ፍንዳታ የደረሰዉ በቅርቡ ህወሓት የሮኬት ጥቃት በፈፀመበት በባሕር ዳር አየር ማረፊያ አካባቢ መሆኑም ታዉቋል። ፍንዳታውን ተከትሎ የጥይት ድምፅ ከተለያየ አካባቢ የተሰማ ሲሆን ተኩሱ ግን ወዲያውኑ መቆሙ ነዉ የተመለከተዉ። የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስት በማሕበራዊ ትስስር ገፁ “ህገወጡ የትህነግ ቡድን ዛሬ ሌሊት 7ሰዓት ከ40 አካባቢ ወደ ባህርዳር ከተማ የሮኬት ጥቃት ፈጽሟል። የሮኬት ጥቃቱ ባህር ዳር ከተማ ላይ ያደረሰው ጉዳት የለም” ሲል ጽፏል፡፡ ዛሬ ንጋት ላይ እንደታዘብነው ኅብረተሰቡ እንደ ቀድሞው ሁሉ በተረጋጋ ሁኔታ  ሰላማዊ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው፡፡ 

ዓለምነዉ መኮንን

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ