1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የህክምና ባለሙያዎች የጦር ግንባር ውሎ

ዓርብ፣ ኅዳር 18 2013

ከአማራ ክልል ወደ ግንባር ሄደው የተመለሱ የጤና ባለሙያዎች ያለ አድሎ ሁሉንም በሙያቸው ሲያገለግሎ መቆየታቸውን አመለከቱ። ባለሞያዎቺ በማካይድራ በሰብዓዊ ፍጡር ላይ የተካሄደዉ ጭካኔ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።  

https://p.dw.com/p/3lvFv
Karte Äthiopien Region Tigray DE

ለሁሉም ወገን የህክምና አገልግሎት ሰጥተናል

 

ከአማራ ክልል ወደ ግንባር ሄደው የተመለሱ የጤና ባለሙያዎች ያለ አድሎ ሁሉንም በሙያቸው ሲያገለግሎ መቆየታቸውን አመለከቱ። ባለሞያዎቺ በማካይድራ በሰብዓዊ ፍጡር ላይ የተካሄደዉ ጭካኔ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።  በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ጊዮን ስፔሻላዝድ ሆስፒታል የአጥንት ህክምና ባለሙያ ዶ/ር አብርሐም አማረ ከህዳር 1ቀን 2013 ዓ. ም ጀምሮ ለ17 ቀናት በግንባር በነበራቸው የህክምና ሥራ ከሁሉም ወገን የመጡ ታካሚዎችን መርዳታቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በፈለገ ሕይወት ሪፍራል ሆስፒታል ነርስ የሆኑት ሰላማዊት አበባውም ህክምናው በሚፈቅደው መሰረት ለሁሉም ወገን የህክምና አገልግሎት መስጠታቸዉን ገልፀዋል፡፡ የዓመት እረፍት ላይ የነበሩት የፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል የድንገተኛ ክፍል ባለሙያ ሲሰተር በላይነሽ ዋለ የእህታቸውን ሰርግ ትተው ግዳጃቸውን በማስቀደም በግንባር ተገኝተው ህክምና መስጠታቸው እንዳስደሰታቸው ሁሉንም ተጎጅ በእኩልነት ማገልገላቸውን ተናግረዋል። የባሕር ዳሩ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባዉን ልኮልናል።

ዓለምነው መኮንን

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ