የሃይማኖቶች ጉባኤ ጥሪ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 27 2013ማስታወቂያ
ኢትዮጵያን የሚያወድመዉን ጦርነትና ፖለቲካዊ ቀዉስ ለማስወገድ ሁሉም ወገኖች የሚሳተፉበት ነፃና ግልፅ ዉይይት እንዲደረግ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠየቀ።ጉባኤዉ ዛሬ እንዳስታወቀዉ ሰሜን ኢትዮጵያ የሚደረገዉ ጦርነት፣ በምዕራብ ኢትዮጵያ ያለዉ ግጭትና በሌሎች አካባቢዎች ያንዣበበዉ ሥጋት በሐገሪቱ ላይ ከፍተኛ ሰብአዊና ምጣኔ ሐብታዊ ኪሳራ አድርሷል።በተገባደደዉ 2013 ዓመት በየአካባቢዉ የተፈጠረዉ ሰዉ ሠራሽና የተፈጥሮ ቀዉሶች እንዲወገዱም ከጵዋግሜ 1 ጀምሮ ለዓምስት ቀን የሚዘልቅ ብሔራዊ ፀሎት እንዲደረግ አዉጇልም።
ሰለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ