1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ«KAAD» ዓውደ ጥናት በአዲስ አበባ

ሰኞ፣ ጥቅምት 26 2011

መደመር የሚለው ሀሳብ በብዝኃነት ላይ ተመርኩዞ አብሮነትን እንደሚያዳብር የካቶሊክ የአካዳሚ ልውውጥ አገልግሎት፣በጀርመንኛው አኅጽሮት ካ አ አ ዴ(KAAD) የአፍሪቃ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ማርኮ ኩን በአዲስ አበባ በተካሄደ ዓውደ ጥናት ላይ አስረዱ።

https://p.dw.com/p/37gZ3
Äthiopien KAAD Konferenz in Addis Abeba
ምስል DW/G. Tedla

የKAAD ዓውደ ጥናት በአዲስ አበባ

ለአዳጊ ሀገራት ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል የሚሰጠው ካ አ አ ዴ ሰሞኑን  ያከበረውን 60ኛ የምስረታ  ዓመት ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ባካሄደው ዓውደ ጥናት ላይ የተገኙ ተሳታፊዎችም ብዙ መልካም ትርጉም  የያዘው የመደመር ሀሳብ ካሁን በፊት የተገፉ እና የተገለሉ የህብረተሰቡን ክፍሎች በመደገፍ  አብሮ ወደፊት ለመራመድ እንደሚያስችል ገልጸዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
አርያም ተክሌ
ተስፋለም ወልደየስ